
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር በአሜሪካ ሎዛንጅለስ እና ካሊፎርኒያ ከተማ ከሚኖሩ የኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር እንደሚወያዩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ግንቦት 3/2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ አምባሳደር ሐመር፣ ከትናንት ጀምሮ እስከ ግንቦት 12 በከተማዋ በሚኖራቸው ቆይታ፣ ከአማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬይና ሱማሊያ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኅበረሰብ ተወካዮች እና ባጠቃላይ ከኢትዮዊያን አሜሪካዊያን ጋር እንደሚወያዩ መስሪያ ቤቱ ገልጧል። የአምባሳደር ሐመርና የኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያኑ ውይይት፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሃት መካከል ፕሪቶሪያ ላይ በተደረሰው ሰላም ስምምነት አፈጻጸ፣ በሌሎች የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች እንዲኹም የኢትዮጵያዊያን ሴቶችን አቅም በመገንባት ዙሪያ ያተኮረ እንደሚኾን መረጃው አመልክቷል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post