በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን አለፈ

በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ አህጉር በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ አፍሪካ) በአህጉሩ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ማለፉን አስታውቋል።
የማዕከሉ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባወጣው የዕለት የኮቪድ-19 ሪፖርት ሰሌዳ እንደሚያሳየው በአፍሪካ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 3 ሚሊየን 238 ሺህ 577 መድረሱን ያመላክታል።
ከነዚህ ውስጥ 78 ሺህ 351 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 2 ሚሊየን 652 ሺህ 326 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።
በቫይረሱ የደቡብ አፍሪካ ቀጣና ክፉኛ የተጠቃ ሲሆን ከዚያ በመቀጠል የሰሜን አፍሪካ አገሮች ላይ ቫይረሱ በስፋት መሰራጨቱ ታውቋል።
በአገር ደረጃ ደቡብ አፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ ግብጽና ኢትዮጵያ በርካታ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባቸው አገሮች ናቸው።
በኢትዮጵያ የዛሬውን ሪፖርት ሳይጨምር እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 130 ሺህ 772 ደርሷል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን አለፈ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply