በአፍሪካ ትልቁ የፊልም ፌስቲቫል በመካሄድ ላይ ነው

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-b233-08db179b7010_w800_h450.jpg

በአፍሪካ ትልቁ ነው የተባለለት የፊልም ፌስቲቫል በቡርኪና ፋሶ መዲን ዋጋዱጉ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የፖለቲካ ትርምስና የእስልምና አክራሪዎች ጥቃት 2 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቿን ባፈናቀለባት ቡርኪና ፋሶ ቅዳሜ የተጀመረው የፊልም ፌስቲቫል ተስፋ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡

“ለሁለት ሣምንታት ሰዎች ይገናኛሉ፣ ሲኒማም አብረው ይመለከታሉ፡፡ የቡርኪና ፋሶ ሰዎች ዓለም እንዳልረሳቸው እንዲረዱ ያደርጋል” ብላለች ቡርኪናቤዋ ተዋናይ ማይሙና ንዳዬ፡፡

ከ15 ሺህ በላይ የሚሆኑ ከናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና አይቨሪ ኮስት የመጡ ጉብኚዎች፣ ተዋናዮችና የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች በፌስቲቫሉ ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

1 ሺህ 300 ፊልሞች ከ 35 የአፍሪካ አገራት ለውድድር የተላኩ ሲሆን 100 የሚሆኑት ለሽልማት እንደታጩ ታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply