በአፍጋኒስታኑ ፍንዳታ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሞቱ

https://gdb.voanews.com/7E0953F0-26D8-40C2-8799-7A8A04CC5FEC_w800_h450.jpg

ዛሬ በአፍጋኒስታን ምስራቃዊ ክፍለ ግዛት በምትገኝ ጃላላባድ ከተማ ውስጥ በደረሱ ሶስት የቦምብ ፍንዳታዎች ቢያንስ ሁለት ሰዎች መሞታቸውና እስከ 20 የሚደርሱ መቁሰላቸውን የታሊባን ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

በፍንዳታው ከተጎዱት መካከል ህጻናትና ሴቶች ይገኙበታል፡፡ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ የለም፡፡

በቅርቡ ከ100 ሰዎች በላይ የሞቱበትና ካቡል አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የደረሰውን የአጥፍቶ ማጥፋት ኃላፊነት የወሰዱት የታሊባን ተቃዋሚ የሆኑት የእስልምና መንግስት ቡድን ተዋጊዎች መሆናቸው ይታወሳል፡፡

የአሁኑ ፍንዳታ የደረሰባት ጃላላባድ የዚሁ እስላማዊ መንግሥት ቡድን ዋነኛ መናኻሪያ መሆኗም ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply