በአፍጋኒስታን 8 የፖሊዮ ክትባት ቡድን አባላት ተገደሉ

https://gdb.voanews.com/B3C1CF78-44E0-4393-B10B-711DDAB248A9_w800_h450.jpg

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት “የነፍስ ማዳን” ሥራ ላይ እያሉ ቢየንስ 8 የፖሊዮ ክትባት ቡድን አባላት በአፍጋኒስታን መገደላቸውን አስታወቀ። ራሚዝ አልክባሮቭ የተሸኙት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ ስር ልዩ ተወካይ፣ ድርጊቱን አውግዘዋል። ታክሃር እና ኩንዱስ በተባሉ የአፍጋኒስታን ክፍለ ሀገራት የደረሱ ጥቃቶችን ዝርዝርም አሰምተዋል።

በአራት የተለያዩ ስፍራዎች በደረሱ “የጭካኔ” ግድያዎች በእጅጉ መደናገጣቸውን የገለጹት አልካባሮቭ “ባለፈው ዓመት ህዳር ላይ ሀገራቀፉ የፖሊዮ ክትባት ከተጀመረ ወዲህ በሰራተኞች ላይ የደረሱ የመጀመሪያዎቹ ጥቃቶች ናቸው” ብለዋል።

ልዩ ልዑኩ የጭካኔ ድርጊቶቹ ሀገሪቱን እያስተባበሩ የሚገኙ የታሊባን ባለሥልጣናት የቤት ለቤት ክትባትን እንዲያስቀሙ እንዳስገደዳቸውም አክለዋል። ለጥቃቱ እስከዚህ ሰዓት ድረስ ኃላፊነቱን የወሰደ የለም።

“ይሄ ትርጉም የለስ የጭካኔ ተግባር መቆም አለበት፣ ፈጻሚዎቹም መመርመር እና ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ድርጊቱ ዓለም አቀፍ የቶርነት ህግን የጣሰ ነው” ሲሉም አክለዋል አላክባሮቭ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply