በኢትዮጲያ ለኩላሊት እጠበት የሚከፈለው የህክምና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ተባለ፡፡ለኩላሊት እጥበት የሚከፈለው የህክምና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ በህመሙ የሚሰቃዩ ዜጎች ችግር ውስ…

በኢትዮጲያ ለኩላሊት እጠበት የሚከፈለው የህክምና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ተባለ፡፡

ለኩላሊት እጥበት የሚከፈለው የህክምና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ በህመሙ የሚሰቃዩ ዜጎች ችግር ውስጥ መናቸው ተነግሯል፡፡

በኢትዮጲያ 5 መቶ ሺህ የሚሆኑ ዜጎች የኩላሊት እጥበት አገልግሎት (ዲያሌሲስ) ያስፈልጋቸዋል ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም፤ በግል የጤና ተቋማት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የኩላሊት እጥበት አገልሎት የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ እንደሚገኝ የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

48 የሚሆኑ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማት መኖራቸውን የገለጹት ዋና ስራ አስኪያጁ ፤ በግብአት እጥረት ምክንያት መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ ቢኖርም ፤ አላግባብ የዋጋ ጭማሪ በኩላሊት እጥበት አገልግሎት ላይ መኖሩ ተመላክቷል ብለዋል፡፡

በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት የግብአት እጥረት እና ለታማሚው የሚያስፈልጉ የመድሃት እጥረቶች ሊከሰት እንደሚችሉ ገልጸው፤ የሚስተዋሉ እግሮችን ለመፍታት ጥረቶችን እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በመንግስት የጤና ተቋማት ላይ አገልግሎቱን ያገኙ የነበሩ ዜጎች በግል የጤና ተቋማት ላይ ህክምናውን ለመከታተል እየተዳረጉ ይገኛሉም ተብሏል፡፡

በግል የጤና ተቋማት ላይ ለአንድ ጊዜ የኩላሊት እጥበት ከ2 ሺህ 6 መቶ እስከ 4ሺህ ብር ድረስ ለአገልግሎቱ እየከፈሉ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡›

በእሌኒ ግዛቸው

መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply