በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለው የቆየ ወዳጅነት በኢኮኖሚውም ዘርፍ መሻሻል እንዳለበት ተገለጸ

በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለው የቆየ ወዳጅነት በኢኮኖሚውም ዘርፍ መሻሻል እንዳለበት ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኤክስፕሎር ኢትዮጵያ ከተሰኘው ተቋም ጋር በመተባበር የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በበይነ መረብ ውይይት አካሂዷል።

በዚህ ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያና የሩሲያን የንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ የቱሪዝምና የባህል ግንኙነት ማሻሻል እንደሚገባ ተነስቷል።

በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለው የቆየ ወዳጅነት በኢኮኖሚውም ዘርፍ መሻሻል እንዳለበት ተናግረዋል።

ከኢትዮ ቱሪዝም እና በሞስኮ የኢትየጵያ አየር መንገድ ተወካይ በኢትዮጵያ ቱሪዝምና በአቪዬሽን መስክ ስላሉ አማራጮች ገለጻ አድርገዋል፡፡

በሩሲያ በኩል የተለያዩ የስራ ሃላፊዎችና ተወካዮች የሁለቱ ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማሳደግ ሰፊ ጥረት መደረግ እንደሚገባው ማሳሰባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተወካይ ስቴፋን ሉግምኖቭ የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ወንድማማች መሆናቸውን በመግለፅ አቢያተ ክርስቲያኖቻቸውም በጋራ የሚደጋገፉ እንዲሆኑ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለው የቆየ ወዳጅነት በኢኮኖሚውም ዘርፍ መሻሻል እንዳለበት ተገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply