”በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከተሳሳተ ግምት የመነጨ ነው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ…

”በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከተሳሳተ ግምት የመነጨ ነው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ…

”በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከተሳሳተ ግምት የመነጨ ነው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ የተስተዋለው የፀጥታ ችግር በተወሰኑ የሱዳን ሚሊሻዎች እና ጥቂት ወታደሮች የተሳሳተ ግምት በመነጨ በድንበር አካባቢ ተኩስ በመክፈታቸው ምክንያት የተፈጠረ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል። አምባሳደር ዲና በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የህወሓት ጁንታ በመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ መንግሥት በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ህግ የማስከበር ሥራ ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጰያ በድንበር አካባቢ ትኩረት አይሰጥም በሚል የተሳሳተ ግምት የተወሰኑ የሱዳን ሚሊሻዎች እና ጥቂት ወታደሮች ካላቸው የተሳሳተ ግምት በመነጨ በድንበር አካባቢ ተኩስ ከፍተዋል ነው ያሉት። ይሁን እንጂ መንግሥት ሙሉ ትኩረቱን በሰሜን የህግ ማስከበር ላይ ቢያደርግም በድንበር አካባቢም የጸጥታ ችግር እንዳይከሰት በትኩረት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። አምባሳደር ዲና ሲቀጥሉ በድንበር አካባቢ ያሉ የሱዳን ሀይሎች ግን “የኢትዮጵያ መንግሥት በድንበር አካባቢ ትኩረት አይስጥም” በማለት በተሳሳተ ግምት የድንበር አካባቢ ህዝባችን ለማጥቃት ተኩስ የከፈቱ ቢሆንም በመከላከያ ሠራዊትና በአካባቢው ሚሊሻ እንደ ኘተመከቱ አስታውቀዋል። የደረሰውን ጉዳት ካለም ወደፊት ተጣርቶ የሚገለጽ ይሆናል ብለዋል ሲል የዘገበው ኢፕድ ነው። አምባሳደሩ ጥቂት ብለው ይግለፁት እንጅ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከምዕራብ ጎንደር ዞን በተለይም የምዕራብ አርማጭሆና የመተማ ወረዳ ነዋሪዎች ለማጣራት እንደሞከረው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሱዳን የመከላከያ ሰራዊት ድንበር ጥሶ በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ኢትዮጵያ እየተጠጋ ስለመሆኑና የባለሀብቶችንና አርሶ አደሮችን ካንብ በኃይል በመቆጣጠር ዝርፊያ እየፈፀመ ስለመሆኑ ነው። የአካባቢው ህዝብም አሳሳቢነቱን በመግለፅ መንግስት በቂ ኃይል አሰማርቶ ሉአላዊነትን እንዲያስከብር፣ ባለሀብቶችንና አርሶ አደሮችን ከጥቃት እንዲታደግ እየጠየቁ ይገኛሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply