በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር አካባቢ የተጠናከረ የፀጥታ ጥበቃና ክትትል እንዲደረግ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ…

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር አካባቢ የተጠናከረ የፀጥታ ጥበቃና ክትትል እንዲደረግ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ…

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር አካባቢ የተጠናከረ የፀጥታ ጥበቃና ክትትል እንዲደረግ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በኩል ድንበር ጥሰው በመግባት የተለያዩ ባለሀብቶችን የእርሻ ካምፖች የሚያቃጥሉ የሱዳን መከላከያዎች በመኖራቸው በአካባቢው የተጠናከረ የፀጥታ ክትትልና ጥበቃ እንዲደረግ ሲሉ ነዋሪዎች አሳስበዋል። የሱዳን ታጣቂዎች በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በኩል ድንበር በመጣስ በእርሻ ኢንቨስትመንት ስራ የተሰማሩትን የአቶ ጋሻው እንዳልክ እና ወ/ሮ አበበችን የእርሻ ካምፖች አቃጥለዋል። ከ2 ቀናት በፊት አምቶኮል ከተባለ ካምፓቸው ተሻግረው የመጡ የሱዳን ታጣቂዎች ወዲቁራ በሚገኘው የአቶ ጋሻው እንዳልክ ካምፕ ላይ ምሽት 5 ሰዓት አካባቢ ዲሽቃ ከመተኮሳቸው በተጨማሪም ቀርበው 2 ትራክተሮችና አንድ መጋዝንን ትናንት አቃጥለው ስለመመለሳቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በረከት ኑሪ አካባቢ ያለውን የወ/ሮ አበበችን የእርሻ ካምፕም ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ማለዳ ላይ ስለማቃጠላቸው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በተመሳሳይ በወዲ ከውሊ የአቶ ሰለሞን በየነን የእርሻ ካምፕ ለማቃጠል ያደረጉት ሙከራ የአካባቢው ሚሊሻና ህ/ሰቡ ደርሶ ባደረገው ጥረት መክሸፉ ተገልጧል። በበረከት አካባቢ አንዲት የእርሻ ካምፕ ሰራተኛ መጋቢን ጨምሮ በርካታ ከብቶችን ዘርፈው ወስደዋል ስለመባሉ ሰምተናልም ብለዋል። በወዲ ከውሊ የመከላከያ ሰራዊት በለቀቀው አንድ ካምፕ ላይም በዛሬው እለት ጉዳት ማደረሳቸው ተገልጧል። በመሆኑም መንግስትም ሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር አካባቢዎች ሰላምና ደህንነትን በማስከበር በኩል ነቅተው እንዲሰሩ ነው መልዕክት የተላለፈው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply