በኢትዮጵያዊነትና በማንነታቸው ዙሪያ ምንም ዓይነት የተድበሰበሰና የተደበቀ አጀንዳ ከሌላቸው ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት ይህችን ሀገር ከገባችበት የፖለቲካ ውጥንቅጥና ማጥ ለማውጣት ቀን ከሌ…

በኢትዮጵያዊነትና በማንነታቸው ዙሪያ ምንም ዓይነት የተድበሰበሰና የተደበቀ አጀንዳ ከሌላቸው ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት ይህችን ሀገር ከገባችበት የፖለቲካ ውጥንቅጥና ማጥ ለማውጣት ቀን ከሌ…

በኢትዮጵያዊነትና በማንነታቸው ዙሪያ ምንም ዓይነት የተድበሰበሰና የተደበቀ አጀንዳ ከሌላቸው ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት ይህችን ሀገር ከገባችበት የፖለቲካ ውጥንቅጥና ማጥ ለማውጣት ቀን ከሌት እየተሰራ መሆኑን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንትና የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ጌጡ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንት እና የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ አብርሃም ጌጡ ጋር በምርጫና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርጓል። አቶ አብርሃም ጌጡ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ባለፉት 30 ዓመታት በተለይም ሕወሓት መራሹ ቡድን በኢትዮጵያ ላይ ሲያደርሰው የነበረውን ወደር የለሽ ግፍ፣ ጭቆና እና ብዝበዛ፣ ገደብ የለሽ ጥላቻን በመቃወም በአቋም ያለምንም ብዥታ በመታገል ቆይቷል ብለዋል። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አደገኛ የሆነው ቡድን ከመንበረ ስልጣኑ እንዲወርድ እና መቀሌ እንዲመሽግ ብሎም አሁን ያለበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ መኢአድ የራሱ አስተዋፅኦና አቋም እንደነበረው አቶ አብርሃም አውስተዋል። ከምርጫ በፊት መቅደም ያለበት ይቅደም በሚል በቅድሚያ ሰላምና ደህንነቷ መረጋገጥ አለበት፣ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ነው፣ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ያሉ ጠላቶችን እንቅስቃሴ ታሳቢ ማድረግም ያስፈልጋል በሚል ላለፉት 2 ዓመታት ተኩልም ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲታገል መቆየቱንም ገልፀዋል። መኢአድ እንደ አንድ አንጋፋ ድርጅት በመላ ኢትዮጵያ አባላትንና ተመራጮችን አዘጋጅተን ምርጫው በትክክል የሚደረግ ከሆነ ከሞላ ጎደል መንቀሳቀስ በምንችልባቸው አካባቢዎች በሙሉ ለህዝባችን ይሆናል የምንለውን ፖሊሲ አርቅቀን በማኒፌስቶ መልኩ ገለጻ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናችን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን ሲሉም አክለው ተናግረዋል። በትግሉ ውጤታማና አሸናፊ ሆኖ ለመውጣትም ተመሳሳይና ተቀራራቢ አጀንዳ፣ ፖሊሲ ካላቸው፣ ለህዝብ፣ለፍትህ፣ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለህግ የበላይነት ከሚሰሩ ፓርቲዎች ጋር መኢአድ አብሮ እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አብርሃም እንደአብነትም ከባልደራስ ጋር ቅንጅት መስርተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። መኢአድ እና ባልደራስም በቅርቡ ከአብን ጋር ተቀራርበውና አብረው በትብብር እየሰሩ መሆናቸውም ተገልጧል። በኢትዮጵያዊነትና በማንነታቸው ዙሪያ ምንም ዓይነት የተድበሰበሰና የተደበቀ አጀንዳ ከሌላቸው ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት ይህችን ሀገር ከገባችበት የፖለቲካ ውጥንቅጥና ማጥ ለማውጣት ቀን ከሌት እየተሰራ መሆኑን የመኢአድ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንትና የውጭ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ጌጡ ተናግረዋል። አንዳንዱ ድርጅት በራሱ አጀንዳ መጭው ሀገር አቀፍ ምርጫ ምንም ዓይነት ችግር እንደማይኖረው፣ መንግስትም ማስተካከል ያለበትን እንዳስተካከለ የሚናገሩ እንዳሉና የእነዚህን ድርጅቶች ሀሳብ እንደማይጋራ ያስታ ቁት አቶ አብርሃም መንግስት አሁንም ለምርጫው ዝግጁነት አለው ብለን አናምንም ሲሉ አክለዋል። እንደአብነት ከሰሞኑ ለብልፅግና በሚል ከተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ያለፉትን ሁለት ዓመታት የበለጠ የሚያስንቅ ነውረኛ የሆነ ተግባር ሲሰሩ ማየታቸውን ገልፀው አንዳንዶች መንግስት ነን ብለው የመንግስት ስልጣን የያዙ፣ አንዳንዶች ደግሞ ከመንግስት ስልጣን ውጭ ሆነው በማይታይና በተሰወረ መልኩ የሀገሪቱ የፖለቲካ ችግር በተያዘው መንገድ እንዳይፈታ የሚያደርጉ ስለመኖራቸው ጠቅሰዋል። ከድጋፍ ሰልፉ ጋር ተያይዞ በብልፅግና አመራሮች የተላለፈውን ፍረጃ ያወገዙት አቶ አብርሃም አብን እና ባልደራስ ብቻ ሳይሆን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መኢአድ ጭምር ነው የተወገዘው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ይህ በብልፅግና ውስጥ የተሰገሰገ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ኃይል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወሳኝ አማካሪ የሆኑትን ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የተወለዱበትን ማንነት ጠቅሶ ጭምር ሲያወገዝ ነበር ያሉት አቶ አብርሃም ምርጫ ቦርድ በሰልፉ ላይ የተላለፉ መልዕክቶችና ፍረጃው ትክክል አይደለም ሲል የሰጠው ውሳኔም ጠንከር ማለት አለበት ብለን እናምናለን ብለዋል። የመኢአድ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንት እና የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ አብርሃም ጌጡ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply