በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍና አካታች ውይይት እዲደረግ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስን ጨምሮ ሰባት የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን የወከሉ አመራሮች ተጠየቁይህንን የጠየቁት ሰባት የተለያዩ…

በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍና አካታች ውይይት እዲደረግ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስን ጨምሮ ሰባት የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን የወከሉ አመራሮች ተጠየቁ

ይህንን የጠየቁት ሰባት የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን የወከሉ አመራሮች ሲሆኑ፤ አመራሮቹ በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ ከተማ ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ጋር በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ምክክር ባደረጉበት ወቅት  ሁሉን አቀፍና አካታች የውይይት መድረክ ተካሂዶ አገሪቱ ከምትገኝበት የፖለቲካ እና የጸጥታ ቀውስ እንድትወጣ ጠይቀዋል።

በብሪቲሽ ካውንስል ተዘጋጀ በተባለው በዚህ የምክክር እና የገለጻ መድረክ፤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ምክትል ሊቀምንበር ዶ/ር ራሔል ባፌ፣ የአረና ትግራይ ፓርቲ ተወካዩ ገብሩ አስራት፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)፣ የእናት ፓርቲ እና የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ተወካዮች እንዲሁም ፖለቲካኛ የሺዋስ አሰፋ በግል ተሳትፈው አዲስ አበባ ውስጥ መቀመጫቸውን ላደረጉ ከ10 በላይ ኤምባሲዎች ገለጻ እና ከወቅታዊ ችግሮች መውጫ የመፍትሄ አቅጣጫ ጠቁመዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply