በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የተደነገገውን የሜዳይ፣ የኒሻን እና የሽልማት አሰጣጥ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል አዋጅ ፀደቀ፡፡በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የተደነገገውን የሜዳይ፣ የኒሻን እና የሽልማ…

በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የተደነገገውን የሜዳይ፣ የኒሻን እና የሽልማት አሰጣጥ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል አዋጅ ፀደቀ፡፡

በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የተደነገገውን የሜዳይ፣ የኒሻን እና የሽልማት አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ በሚያስችለው በዚህ ረቀቅ አዋጅ ላይ ውይይት ካደረገ በኃላ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል፡፡

የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ይህንን የኒሻን እና ሜዳይ ሽልማትን በተመለከተ ውይይት እና አስተያየት ከተደረገበት በኃላ አዋጁ እንዲፀደቅ ጠይቀዋል፡፡

በዚህም የምክር ቤቱ አባላት የሜዳይ፣ የኒሻን እና የሽልማት አሰጣጥ ስርዓትን በተመለከተ ያለውን አዋጅ በሙሉ ድምፅ እንዲፀድቅ ተደርጓል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔውን ያሳለፈው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6 2016 ባደረገው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 26ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

የሜዳይ ወይም ኒሻን ተሸላሚ የሚሆኑ አካላት በህዝብ መገልገያ ቦታዎች ላይ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል እንዲሁም ከእዚህ ዓለም በሚያርፉ ግዜ በክብር እነዲሸኙ የሚያስችልም አዋጅ የተካተተበት መሆኑ ተገልፃል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply