በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራችው “ፀሐይ” የሚል መጠሪያ የተሰጣት አውሮፕላን ትናንት ምሽት ላይ አዲስ አበባ መድረሷ ተነግሯል።

በጣሊያን ተወስዳ የነበችረው አውሮፕላን ባሳለፍነው ሳምንት ለኢትዮጵያ ተመልሳ መሰጠቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።

በፈረንጆቹ በ1935 በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ ተገጣጥማ በረራ ያደረገችው ፀሐይ አውሮፕላን ከበርካታ ዓመታት በኋላ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ደርሳለች።

ከጣሊያን ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰችው “ፀሐይ” አውሮፕላን በ”አድዋ ድል መታሰቢያ” እንደትቀመጥ መደረጉም ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ፀሐይ” አውሮፕላንን በዛሬው ዕለት ተረክበው በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለጎብኝዎች ምቹ በሆነ ስፍራ ማኖራቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

አውሮፕላኗ “ፀሐይ” የሚለውን ስያሜውም የቀዳማዊ ኃይለስላሴን ልጅ ልዕልት ፀሐይን ለማሰብ የተሰጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply