በኢትዮጵያ   ለመጀመሪያ  ጊዜ  የኢኮኖሚ  ድርጅቶች  ቆጠራ   በቅርቡ  ይካሄዳል ተባለየኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት   የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ እና  የተቀናጀ የቤተሰብ ፍ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/a8nl03-9It3Z35MyTNLgu8WbP2fMTrye5BDFVLjR6hGcMXkLHU2fk7YQdvWj-HvsD9KJSGGmpMaeN5POFJCN0y5IphxkKui6I9xhzpAdPGUWJu0OGajRvKAFqDKJgVWvlvRsCqqNcreh-zfbN9gYOMv1lThfDYM9MZIn0Lznai99Q7N7Aem6WAscd0qLWFE0sq9LkjjrvzvaHKvxgB1YUrQo5aZ78_qnvqjOsmlJ88_V9yvhIxcjsDpJ0YL3-aHp4cf-VL0NdooQz1_7QEPDENPBugUaRR89-Zs-G0iRN2NaMfutUN088AC_fTU1G1HEEpZSkZTYfdvuCthGY0zDMw.jpg

በኢትዮጵያ   ለመጀመሪያ  ጊዜ  የኢኮኖሚ  ድርጅቶች  ቆጠራ   በቅርቡ  ይካሄዳል ተባለ

የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት   የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ እና  የተቀናጀ የቤተሰብ ፍጆታ ጥናት ለመጀመሪያ ጊዜ በቅርብ ጊዜያት  ለማድረግ መታቀዱን አስታውቋል ።

የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊና የመረጃ ስርጭት ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት    በኢትዮጵያ  ለመጀመሪያ ጊዜ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ እንደሚካሄድ ተናግረዋል ።

በዚህም  ከትልልቅ ድርጅቶች እስከ ትንንሽ መንገድ ላይ እስካሉ የኢኮኖሚ ተቋማት በቆጠራው ይካተታሉ ብለዋል።

ከኢንዱስትሪ ሚኒስትር ጋር በጋራ እንደሚሰራና ለኢንዱስትሪ ፖሊሲ ቀረፃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም  ገልጸዋል።

አምስተኛው ዙር የሥነ ሕዝብና ጤና ዳሰሳ ጥናት  በተያዘው በጀት አመት በመጪው ሃምሌ ወር እንደሚጀመር ያነሱት ሃላፊው የእሱን ማለቅ ተከትሎ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ እንደሚጀመርም ነግረውናል ።

ይህ ቆጠራ  ከሌሎቹ ቆጠራ  ለየት ባለመልኩ  ብዙ ጥናት እና ጊዜ እንደሚወስድ  ሃላፊው ገልጸው    የእንዚህ የኢኮኖሚ ድርጅቶች መቆጠር ለኢንዱስትሪም ይሁን ለገነዘብ ሚኒሲተር ትልቅ ግብዓት እንደሚሆንም   ተናግረዋል።

ሁሉንም ጥናቶች እስከ  2018 ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙን አቶ ሳፊ ገመዳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም  ገልፀዋል።

ለአለም አሰፋ

ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply