በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የአለም አቀፍ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ቀን ሊከበር ነው፡፡በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፈረንጆቹ ግንቦት-4 የሚከበረው የእሳት አደጋ ሠራተኞች ቀን ለመጀመርያ ጊ…

በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የአለም አቀፍ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ቀን ሊከበር ነው፡፡

በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፈረንጆቹ ግንቦት-4 የሚከበረው የእሳት አደጋ ሠራተኞች ቀን ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሊከበር መሆኑን ሰምተናል፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያዉ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ይህ ቀን መከበሩ የሰውን ህይወትና ንብረት ለመታደግ ሲሉ የህይወትና የአካል መስዋዕትነት ለሚከፍሉት ለአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ትልቅ የሞራል ስንቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ህብረተሰቡና መንግስት የአደጋ መቆጣጠር ስራን በጥልቀት ተረድተው ለመደገፍና ተገቢውን ከበሬታ ለመስጠት ያስችላቸዋል ሲሉም አክለዋል፡፡

የእሳት አደጋ ሠራተኞች ቀን መከበር የጀመረው በፈረንጆቹ 1999 አውስትሪያሊያ ቪክቶሪያ ሊንቶን ውስጥ በተነሳው የሰደድ እሳት ቃጠሎ ምክንያት፣ የሰው ህይወትና ንብረት ለማዳን ሲሉ 5 የእሳት አደጋ ሰራተኞች በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን ማጣታቸው ከተሰማ በኋላ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ያደረገውም አውስትራሊያዊ ጄጄ ኢደሞንድሴን እንደነበረ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡
የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቀን ሲከበር ጥቅም ላይ የሚውለው ሪቫን ቀለም ቀይና ሰማያዊ ቀለም ያለው ምልክት ነው፡፡

ለዚህ እለት መከበር ሚናቸውን የተወጡት ጄጄ ኤድሞንድሰን ይህ ቀለም ሲመርጡ ምክንያታቸው ቀይ ቀለም እሳትን የሚያመለክት ሲሆን ሰማያዊው ቀለም ደግሞ ውሃን እንደሚወክል ያስርዳሉ፡፡

በዚህም መነሻ ቀይ በሰማያዊ የሆነው ሪቫን ቀለም የአለም አቀፍ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቀንን እንዲወክል ሆኗል፡፡

በዚህ ምክንያት በአብዛኛው ሰዎች ይህንን ሪቫን በመኪኖቻቸው ፣ በሸሚዞቻቸው፣ በመስኮቶቻቸው እንዲሁም በአካባቢያቸው በሚገኙ ዛፎች ላይ በመስቀል ቀኑን ያከብሩታል፡፡

ይህንን ሪቫን በተለያዩ መንገድ መጠቀም ለእሳት አደጋ ሰራተኞች ያለንን ድጋፍና ፍቅር መግለጫ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሚያዝያ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply