You are currently viewing በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበርና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተባባሪነት ከአማርኛ ወደ ጉምዝኛ ቋንቋ የተተረጎመው  መጽሐፍ ቅዱስ ተመረቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበርና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተባባሪነት ከአማርኛ ወደ ጉምዝኛ ቋንቋ የተተረጎመው መጽሐፍ ቅዱስ ተመረቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበርና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተባባሪነት ከአማርኛ ወደ ጉምዝኛ ቋንቋ የተተረጎመው መጽሐፍ ቅዱስ ተመረቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበርና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማካኝነት የተተረጎመው አዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ተመርቋል። መጽሐፉ ከአማርኛ ወደ ጉምዝኛ ቋንቋ የመተርጎሙ ዋና ዓላማ የጉሙዝ ማህበረሰቦች በቋንቋቋቸው ሐይማኖታቸውን ተምረውና ተረድተው መንግስተ ሰማያትን እንዲወርሱ ማድረግ መሆኑን በምረቃ ስነ ሥርዓቱ ተብራርቷል። ስምንት ዓመታትን የፈጀው ይህ የመጽሐፍ ትርጉም የቋንቋዎች ተመሳሳይ የአጻጻፍ ስርአትና የጉምዘኛ ቋንቋ የቁልፍ ቃላት መፍቻ አለመኖር ረጅም ጊዜ እንዲወስድ እንዳደረገው በምረቃ ስነ ስርዓቱ ተገልጿል። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የባሕር ዳር ፣ የደሴና የመተከል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፅዑ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ እንዳሉት የትርጉም ሥራውን ረጅም ጊዜ ወስደው ለሠሩ አካላትና ለደገፉ የሲቪክ ማህበራትን አመስግነው መጽሐፉ ወደ ምዕመኑ እንዲደርስና እንዲጠቀሙበት ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል። የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር የሰው ሃብት አስተዳደር የጠቅላይ ፀሐፊ ተወካይ አቶ ተካበ ነዋይ ለጉሙዝ ማህበረሰብ ትልቅ ደስታናን የፈጠረ ነው ብለዋል። መጽሐፉ ተተርጉሞ ለማህበረሰቡ እንዲቀርብ ላደረጉ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበርና ሌሎች ተባባሪ ተቋማትና ግለሰቦችን በማመስገን ትልቅ ደስታ እንደፈጠረላቸው የምረቃው ተሳታፊዎች ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የመተከል ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ፀጋዬ አበበ መጽሐፉ የእግዚያብሔር እስትንፋስ ስለሆነ ለነፍሳችን መዳኛ እንድንጠቀምበት ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ በበኩላቸው የበለጠ የሚያቀራርበንና ላጠፋነው ጠፋት ፈጣሪን ጠይቀን ምኅረት የምናገኝበት ስለሆነ ዛሬ የተመረቀው መጽሐፍ ለጉምዝ ማህበረሰብ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በመጠቆም እንኳን ደስ አለን አላችሁ ብለዋል። በመጽሐፍ ምረቃው ሥነ ስርዓት ላይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት አባቶችና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች ቤተክርስቲያን የሐይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች ፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች መገኘታቸውን የማንዱራ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው የዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply