በኢትዮጵያ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ ተዘጋጀ በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ መዘጋጀቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።ጤና ሚኒስቴር እንዳስታ…

በኢትዮጵያ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ ተዘጋጀ

በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ መዘጋጀቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከሆነ መመሪያውን ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ ከግብርናና ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ከተለያዩ የስነ-ምግብ ላይ ከሚሰሩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር እንደተዘጋጀ ተነግሯል።

በዚሁ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያን ይፋ ለማድረግ ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፤ ከትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ከግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ የሆኑት ዶ/ር ፍቅሬ ረጋሳ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የክልል ጤና ቢሮ ሃላፊዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እና በስነ-ምግብ ዙሪያ የሚሰሩ አጋር ድርጅቶች በተገኙበት ነው ይፋ የተደረገው።

ይህ መመርያ መዘጋጀቱ ምግብን እንዴት ማግኘት እንደሚቻልም የሚገልጽ መሆኑም የጤና ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

ይህን መመርያ ለማዘጋጀት የተለያዩ ሴክተሮች የተካተቱበት መሆኑን አንስተው ከ25 በላይ ከፍተኛ ባለሙያዎች መካፈላቸው አስታውቀዋል።

እርሳቸው እንዳሉት ከሆነ መመርያው ከአመጋገብ ጋር ለሚመጡ ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ያስችላል ብለዋል።

በአፍሪካ የአመጋገብ መመርያ ካላቸው ስምንት አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗንም ጠቅሰዋል ዶ/ር ሊያ፡፡

በዚሁ መድረክ ንግግር ያደረጉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መመሪያው አስፈላጊነቱን በማንሳት በትምህርት ሚኒስቴርም አጋዥ የሆኑ ስራዎች መጀመራቸውን አንስተዋል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር እቅድ ከዚህ በኃላ የሚከፈቱ ሁሉም አዲስ ትምህርት ቤቶች የተወሰነ የእርሻ ቦታ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።

ይህ በመደረጉ ተማሪዎቹ የእርሻ ልምድ እንዲኖራቸው ከማድረግ ባሻገር ትምህርት ቤቱ በራሱ እንዲቆሙ የሚያደርግ መሆኑን ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል።

ረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 07 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply