You are currently viewing በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ብዛት 25.3 ሚሊዮን መድረሱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ በየዓመቱ እየተባ…

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ብዛት 25.3 ሚሊዮን መድረሱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በየዓመቱ እየተባ…

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ብዛት 25.3 ሚሊዮን መድረሱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በየዓመቱ እየተባባሰ በቀጠለው ዘርፈ ብዙ ችግር እየተፈተነች የምትገኘው ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ እየበረታባት መምጣቱን ተከትሎ፣ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገልጿል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም ዓቀፍ የሕጻናት ነፍስ አድን ፈንድ (ዩኒሴፍ)፣ ስለ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ሁኔታ አዲስ ባወጣው ሪፖርት፣ ሰብዓዊ ድጋፍ ከሚሹ 25.3 ሚሊዮን ሰዎች መካከል 13.3 ሚሊዮን ያክሉ ሕጻናት ናቸው ብሏል፡፡ ባለፈው የፈረንጆቹ 2022 በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቁጥር 22 ሚሊዮን ደገማ የነበረ ሲሆን፣ በተያዘው 2023 በመጀመሪያ ኹለት ወራት ብቻ ከ25 ሚሊዮን በላይ ተሸግሯል፡፡ በተለያዩ ችግሮች የሰው እጅ ጠባቂ የሆኑ ዜጎች በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ 4.51 ሚሊዮን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ናቸው፡፡ በሰው ሰራሽ እና በፈተጥሮ ችግሮች ከቤት ንብረታቸው ከተፈናቀሉ ዜጎች በተጨማሪ፣ በቤታቸው ሆነው ሰብዓዊ ድጋፍ የሚጠበቁ በርካታ ናቸው ተብሏል፡፡ የዩኒሴፍ ሪፖርት እንደሚያመላክተው፣ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በኢትዮጵያ አስቸኳይ ሰብአዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት 674.3 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል። ድጋፉ በአየር ንብረት መዛባት ምክንያት በተከሰተው ድርቅ መስፋፋት፣ በጦርነትና ግጭት በአግባቡ ምርት መሰብሰብ ባለመቻሉ፣ በሰሜኑ ጦርነት ለችግር የተጋለጡ ዜጎች መበራከት፣ በመላ አገሪቱ የምግብ ዋስትና ዕጥረት ለገጠማቸው እና በህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎቱ ጨምሯል፡፡ ለድጋፍ የሚያስፈልገው ገንዘብም በተመሳሳይ የጨመረ ሲሆን፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ወጪው ከባለፈው 2022 ፍጆታ የ142 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ጭማሪን አሳይቷል፡፡ ለ2023 ከሚያስፈልገው ሰብዓዊ ድጋፍ ወጪ ውስጥ 22.8 ሚሊዮን ዶላር ብቻ የተገኘ ሲሆን፣ ይህም የሕይወት አድን ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ከሚያስፈልገው ገንዘብ 11 በመቶውን ብቻ ይወክላል ነው። የተለያዩ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለሰብዓዊ ድጋፍ ገንዘብ እየለገሱ ቢሆንም፣ የህይወት አድን ሥራውን ለማስፋት ለረጂ አካላት ዩኒሴፍ ተማጽኖ አቅርቧል፡፡ አዲስ ማለዳ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply