በኢትዮጵያ ሶስተኛው ማዕበል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 በኢትዮጵያ ሶስተኛው ማዕበል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴሩ የኮቪድ-19 ምላሽ አስተባባሪ አቶ መብራቱ ማሴቦ ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት ላለፉት ስምንት ሳምንታት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል። የወረርሽኙ ማዕበል በተለይ ደግሞ ከሀምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ጀምሮ መጠነኛ መቀነስ አሳይቶ እንደነበረ መግለጻቸውን ኢትዮጰያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

ይሁን እንጂ  በነሐሴ ወር እንደ አዲስ ማገርሸቱንና በዚህም ከ600 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ አስተባባሪው ጠቁመዋል። በ24 ሰዓታት ውስጥ በሚደረግ የላቦራቶሪ ምርመራ እስከ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ቫይረሱ እየተገኘባቸው መሆኑ ነው የተገለጸው። በቫይረሱ የተያዙ ነገር ግን  ምልክቱን ያላሳዩና ያልተመረመሩ በርካታ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉና የምርመራ አቅም ውስንነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር
ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችልም አቶ መብራቱ አስታውቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply