You are currently viewing በኢትዮጵያ በመንግስት ድጎማ የሚቀርበው የአንድ ኩንታል ማዳበሪያ ዋጋ ከ1800 ብር ወደ 4500 ብር (250%) ጭማሪ አሳይቶል።ችግሩ በአማራ አርሶ አደሮች ዘንድ የከፋ እንደሆነ እየተነገረ…

በኢትዮጵያ በመንግስት ድጎማ የሚቀርበው የአንድ ኩንታል ማዳበሪያ ዋጋ ከ1800 ብር ወደ 4500 ብር (250%) ጭማሪ አሳይቶል።ችግሩ በአማራ አርሶ አደሮች ዘንድ የከፋ እንደሆነ እየተነገረ…

በኢትዮጵያ በመንግስት ድጎማ የሚቀርበው የአንድ ኩንታል ማዳበሪያ ዋጋ ከ1800 ብር ወደ 4500 ብር (250%) ጭማሪ አሳይቶል።ችግሩ በአማራ አርሶ አደሮች ዘንድ የከፋ እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል። ችግሩን የጎላ ካደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች ጥቂቶቹ፦1) ምርታቸውን በቅናሽ የዋጋ ጣሪያ ተመን እንዲሸጡ በማስገደድ የመንግስት በነፃ ገበያ ጣልቃ መግባት፥ ወጪያቸውን ሊሸፍን የሚችል ገቢ ሊያገኙ አልቻሉም፤አማራ ክልል የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ በአማካኝ ….$100(5000. ብር) ሲሆን፥በውጭው አለም (በጥቁር ገበያ እየወጣ) ግን እስከ $500(25,000 ብር) ይሸጣል።የአማራ ገበሬዎች ጤፍ export ማድረግ አይችሉም። 2) ግብር፦ ከሌላው የሃገሪቱ አርሶአደሮች በተለዬ ሁኔታ ለፌደራል መንግስትና በክልሉ መንግስት ባለቤት ለሆነው “አልማ” ለተሰኘ ድርጅት… ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ መገደዳቸው፤ የማዳበሪያ እዳቸውን እንዳይከፍሉ አቅማቸውን ማዳከሙ ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ፥ በተለይ የማዳበሪያ ዋጋ አለአግባብ መጨመር ምክንያት ፥ አርሶአደሮች አቤቱታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። 3) ሜካናይዝድ የሆነ የእርሻ ስነዘዴ ትምህርት፥ መሳሪያ፥ እና ግብአቶች አለመመቻቸት፥ ደግሞ ችግሩ ቀጣይነት እንዲኖረው ቁልፍ ምክንያት ሆኗል። መፍትሄዎች፥ 1) የማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋክቶሪ መገንባት 2) የግብርና ማሽኖች፥ ምርጥ ዘር አቅርቦት፥ እና ሌሎች ግብአቶች ላይ መዋለ ንዋይ ማፍሰስ፤ 3) የነፃ ገበያ ዕድል መክፈት እና መረጃ መስጠት፤ 4) ለአርሶአደሮች አስፈላጊው ድጎማና ድጋፍ ማድረግ፥ የአልማ የተባለ ድርጅት የሚሰበስበውን አግባብ ያልሆነ ግብር እንዲያቆም አጥብቆ መታገል ተገቢ ነው ሲል አማራ ኢኮኖሚክ ቲንክ ታንክ በገጹ አስፍሯል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply