በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በየጊዜው እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር  ገለፀ፡፡

በተለይም በአማራ፣ኦሮሚያ፣ቤንሻንጉል እና ሌሎች ክልሎች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በየጊዜው እየተፈፀሙ መሆኑን ሚኒስቴሩ አንስቷል፡፡ማንነትን መሰረት በማድረግ በሚፈፀሙ ጥቃቶች ንጹሃን እየሞቱ እና ሴቶች ዘግናኝ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን በየጊዜው የሚደመጥ ሆኗል፡፡

በዚህም ረገድ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉት የጥፋት ሀይሎች እያደረሱ ያለውን ዜጎችን የማፈናቀል እና የመግደል ተግባሮችን ለማስቆም እየተሰራ መሆኑን በሚኒስቴሩ የወንጀል ክትትል እና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ለማ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡

በተለይም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዳንጉራ ወረዳ ከሰሞኑ ጥቃት የፈጸሙ አካላትን የመከላከያ ሃይል ኮማንድ ፖስት መደምሰሱን እንደማሳያነት አንስተዋል፡፡በአማራ ክልል እየተሰተዋሉ ከሚገኙ ጥቃቶች ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር በሰላማዊ መንገድ እና ህግን መሰረት አድርጎ መቆጣጠር የሚለውን የፌዴራል መንግስት አቋምን የክልሉ መንግስት እየተቸው ይገኛል፡፡

ሆኖም የፌደራል መንግስት ያለ ህግ አግባብ እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው ብሎ እንደማያምን የገለጹት አቶ መንግስቱ፤ ሚኒሰቴሩ የሚወሰደውን የህግ አካሄድም አብራርተዋል፡፡

ቀን 25/07/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

  1. Bekele Gebre

    Useless and meaningless propoganda. Where have you been when genocide committed on poor Amhara children, mothers and elderly? Now you came out to defend your killer bosses and blame the killed ones. Useless ministry.

Leave a Reply