በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ተደጋጋሚ በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማስቆም ምክንያቱን መረዳት እና መፍትሄው ላይ መስራት እንደሚገባ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መደጋገም እና የንጹሃን ዜጎች ሞትና ስደት መከተልን ከወዲሁ መቀነስ ካልተቻለ ከባድ ፈተና ሆኖ ሊቀጥል ይችላል ሲሉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ለአሐዱ ተናረዋል፡፡አሁን እየታየ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሷል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ቁርጠኛ የሆነ የፖለቲካ ውሳኔን የሚፈልግ ጉዳይ ነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በተለያዩ አካባቢዎች በተደጋጋሚ በንጹሃን ላይ የሚደርሰውን ግፍ፣ በደል እና ወንጀል ለማስቆም መፍትሄው ላይ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡ችግሩን ከመሰረቱ ለመቅረፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን ዋነኛ ምክንያት መርምሮ ማግኘት ብሎም ፈጥኖ ምላሽ መስጠት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ቀን 05/06/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ተደጋጋሚ በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማስቆም ምክንያቱን መረዳት እና መፍትሄው ላይ መስራት እንደሚገባ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገልጿል፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply