በኢትዮጵያ በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት እንዲቆም የሚጠይቅ የርሃብ አድማ በለንደን መካሄድ ከጀመረ 3ተኛ ቀኑን ይዟል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም…

በኢትዮጵያ በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት እንዲቆም የሚጠይቅ የርሃብ አድማ በለንደን መካሄድ ከጀመረ 3ተኛ ቀኑን ይዟል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በእንግሊዝ ለንደን አማራዎችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የጀመሩት የርሃብ አድማ ዛሬ 3ኛ ቀኑን ይዟል። ከተለያዩ ሀገራት ወደ ዩኬ ለንደን ያቀኑ አማራዎችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በአማራ ላይ የቀጠለውን የዘር ፍጅት እያወገዙ ይገኛሉ። የስቶፕ አማራ ጄኖሳይድ ዳይሬክተር ዮዲት ጌዲዮንን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት ወደ ለንደን ያቀኑ አማራዎችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ብርቱ ሴቶች የርሃብ አድማውን ለ3ተኛ ቀን እያደረጉ ይገኛሉ። ከመካከላቸውም በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው መዋቅራዊ የዘር ፍጅትን ለማውገዝ ሰው መሆን በቂ ነው ያሉ የጉራጌ ልጆች የርሃብ አድማውን እያካሄዱ ነው። በአማራ ላይ የቀጠለው የዘር ፍጅት ይቁም! Stop Amhara Genocide in Ethiopia!

Source: Link to the Post

Leave a Reply