በኢትዮጵያ በኤች አይ ቪ ከተያዙ ሰዎች ዉስጥ ግማሽ ያህሉ ህይወታቸዉ ማለፉ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠርያ ፅ/ ቤት እንዳለዉ በኢትዮጵያ ባለፉት 40 ዓመታት ከ 74 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኤች አይ ቪ ተይዘዋል፡፡

ከነዚህ ዉስጥም 36 ሚሊዮን ወይም ለግማሽ የተቃረበ ቁጥር ያላቸዉ ሰዎች ለሞት መዳረጋቸዉ ታዉቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠርያ ፅ/ ቤት እንዳለዉ፣ከቫይረሱ ጋር እንዳሉ ታውቀው ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙት 62 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸዉ፡፡

በኢትዮጵያ ካሉ ክልሎች በስርጭት መጠን ሲታይ ጋምቤላ 4.45 በመቶ ፣ አዲስ አበባ 3.42 በመቶ እንዲሁም ድሬዳዋ 3.12 በመቶ በመሆን ከፍተኛዉን ደረጃ የያዙ በሚል ተቀምጠዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
መስከረም 04 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply