በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ9 ሺህ 38 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሺህ 138 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በቫይረሱ 37 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ ደርሷል፡፡

ከዚህ ባለፈም አሁን ላይ 862 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት፡፡

1 ሺህ 54 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

The post በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ ደረሰ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply