በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከቻይና በላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡በኮሮና ቫይረስ የማቾች ቁጥር ኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተነሳባት ቻይና መብለጧን ቁጥራዊ መረጃዎች ያሳያሉ…

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከቻይና በላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በኮሮና ቫይረስ የማቾች ቁጥር ኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተነሳባት ቻይና መብለጧን ቁጥራዊ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በኢትዮጵያ በኮቪድ19 የሞቱ ዜጎች ቁጥር ከ5ሺህ የበለጠ ሲሆን በቻይና በቫይረሱ የሞቱ ዜጎች ደግሞ 4ሺህ 636 ብቻ ነው፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በሶስቱ ቀናት ብቻ 176 ያህል ዜጎች በቫይረሱ አማካኝነት ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ይሕ ቁጥር ወደ ህክምና ጣቢያዎች መጥተው የሞቱትን ብቻ የሚያሳይ ሲሆን የህክምና ጣቢያ ሳይመጡ በቫይረሱ እንደተጠቁ ሳያውቁ በየቦታው በወረርሽኙ የሞቱ ወገኖች አጅጉን ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ነው የተባለው፡፡

በትላንትናው እለትም የ43 ዜጎች ህይወት ሲያልፍ 700 ያህል ዜጎች ደግሞ በጽኑ ህሙማን ክፍል ይገኛሉ ተብሏል፡፡
ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ በሀገር ደረጃ ብዙ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ሁሉም የበኩሉን መወጣት አለበት ተብሏል፡፡
በአሁኑ ሰአት የመተንፈሻ መሳሪያዎች እጥረት እያጋጠመ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው፡፡

የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ማእከል ሲዲሲ ባስጠናው ጥናት መሰረት ያልተከተቡ ሰዎች ከተከተቡት ጋር ሲነጻጸር በቫይረሱ የመያዝ እድላቸው ከ4.5 እጥፍ በላይ ነው ይላል፡፡ ይህ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በዋነኝነት ክትባት መውሰድ አማራጭ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

እንደዚሁም ሆስፒታል የመግባት አድላቸው ከ10 እጥፍ በላይ እንደሆነ እና ታመው የመሞት እድላቸው ደግሞ 11 እጥፍ ነው ሲል አስታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መስከረም 12 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply