በኢትዮጵያ በኮቪድ የመያዝ መጠን በ12 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገለፀ።

በጤና ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ሀላፊ የሆኑት ዶክተር ተገኔ ረጋሳ ማህበረሰቡ ጋር ያለው መዘናጋት አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ምክንያትም በኮቪድ የመያዝ መጠን በ12 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጎታል ነዉ ያሉት፡፡

የሶስተኛው ዙር የኮቪድ 19 ክትባት ለ22 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሰዎች መሰጠቱን የገለጹት ሀላፊው ፣23 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሰዎችን ለመከተብ ታቅዶ 22 ነጥብ 4 ሚሊዮኑ ተከትቧል ብለዋል።
ይህም የእቅዱን 89 በመቶ ማሳካት መቻሉን ያሳያል ብለዋል፡፡

18 ሚሊዮን ዜጎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት የወሰዱ መዉሰዳቸዉን የተናገሩት ሃላፊዉ ቀሪው ደግሞ ሙሉውን ክትባት የወሰዱ ናቸው።

በኦሮሚያ ፣አማራ እንዲሁም በደቡብ ክልሎች ጥሩ የክትባት አፈፃፀም እንዳላቸው የተገለፀ ሲሆን ፤ አዲስ አበባ፣ ሀረር እና ድሬዳዋ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያሳዩ መሆናቸዉንም ሃላፊዉ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ የክትባት አፈፃፀሙ ዝቅተኛ የሆነበት ምክንያት ዘግይቶ በመጀመሩ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከ70 በላይ ዜጎች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ የገለፁት ዶክተር ተገኔ፣ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ መመሪያዎችን በአግባቡ እንዲተገብር አሳስበዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply