በኢትዮጵያ በዓመት 10 ሺህ የሚሆኑ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡
ዩኒሴፍ ባስጠናው ጥናት መሰረት በኢትዮጵያ 10 ሺህ የሚጠጉት እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተገልጿል፡፡
እናቶች ህይወታቸውን እንዲያጡ ምክንያት ናቸው የተባሉት አንደኛው እና ዋነኛው በቤት ውስጥ መውለድ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የቤተሰብ እቅድ በተለያየ አጋጣሚ ማግኘት ባለመቻላቸው እንደሆነ አመላክቷል፡፡
እንደ ዩኒሴፍ ገለጻ፣ ከሚወልዱ እናቶች መካከል 50 በመቶ የሚሆኑት ብቻ በጤና ተቋማት ይወልዳሉ፡፡
በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን