በኢትዮጵያ በዝናብ ምክንያት 300 ሺህ ዜጎች ለችግር ተጋልጠተዋል ሲል ዩኒሴፍ አስታወቀ፡፡

በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ 300ሺህ ያህል ዜጎች በዝናብ ምክንያት ለችግር መጋለጣቸው ዩኒሴፍ አስታውቋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ እንዳሳወቀው በኢትዮጵያ በሰብአዊ እርዳታ ዙርያ በትላንትናው እለት ባወጣው ሪፖርት በዝናብ ምክንያት በሃገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ለችግር መጋለጡን አስታውቋል፡፡

ዩኒሴፍ ሃሙስ እለት ባወጣው የሰብአዊ እርዳታ ሪፖርት ላይ እንዳስታወቀው በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ በአፋር ክልል በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንደጎዳ እና የኩፍኝ እና የዴንጊ ትኩሳትን ጨምሮ ተላላፊ በሽታዎች ስርጭት ከፈተኛ ደረጃ ላይ እንደደረሱ አሳስቧል፡፡

በክልሉ ያጋጠመው የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከትሎ በርካታ ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው ድርጅቱ የለጸው፡፡

እንደዚሁም በክልሉ ከ20 በላይ የውሃ ገንዳዎች በዝናቡ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ዜጎች የንጹህ ውሃ አቅርቦት እያገኙ አይደለም ብሏል፡፡

በዚህ የጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ዜጎች የሚሆን 674ሚሊዮን ዶላር የሚያስፈልግ ሲሆን አሁን ላይ ከለጋሽ ድርጅቶች የተገኝው 9በመቶ ብቻ ነው ሲል ዩኒሴፍ ገልጧል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 07 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply