በኢትዮጵያ በየአመቱ በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ከ5ሺህ 300 በላይ ሴቶች እንደሚሞቱ ተገለጸ።በኢትዮጵያ በየአመቱ በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሴቶች (እናቶች) የሚ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/vG7mxGAPS0k9udDTRD9kyVimuUeV0Z5vRBf3WtcrLwP4GdJSMyS7stCivmdwjgrC8cGTxwWEjB9u9QFFD3i6-FfQ6G0zZn1KoVRUvq3RY2l8BpG4J-HqL14rGeGmr4TKHc8M90lUt6D54BqzwLmeMVUKdMb3gwrJaBHt9BV2ZhfvzS8wKBd3DJ-ZVQMRPFjRProeVOKJNg2MbUHjtTmbydIEyaT5ksS9n0o67HQUw5luZttl0aVoRF_BhWWXnskQ33OGESnyswgpsWD5jF656n7p3QoVKZIqpnxIM_sIXDEn16zkF5rREsYw7_kSqmo0E-fmN75MkQK0i3ELPCjXwg.jpg

በኢትዮጵያ በየአመቱ በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ከ5ሺህ 300 በላይ ሴቶች እንደሚሞቱ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ በየአመቱ በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሴቶች (እናቶች) የሚያዙ ሲሆን ከ5ሺህ 300 በላይ ሴቶች ደግሞ ለሞት ይዳረጋሉ ተብሏል።

በኢትዮጵያ ከ 7 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሴቶች (እናቶች) በየአመቱ በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር የሚያዙ ሲሆን ከ5ሺህ 300 በላይ የሚጠጉ ሴቶች እንደሚሞቱ በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ታከለች ሞገስ ለ ኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል ።

በግብረ-ስጋ ግንኙነት ጊዜ ከሰው ወደ ሰው በሚተላለፈው ሂውማን ፓፒሎማ በተባለ ቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን 80 በመቶ የሚሆኑ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ታማሚዎች ህመሙ ስር ከሰደደ በኃላ ወደ ጤና ተቋማት እንደሚሄዱ ተናግረዋል።

በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው የግንዛቤ እጥረት እና የቅድመ ካንሰር ምርመራ አለማከናወን እንደ መነሻ ምክንያት ይነሳል ብለዋል።

በአለማችን በየአመቱ 600 ሺህ የሚሆኑ ሴቶች በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር እንደሚያዙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በማህፀን ጫፍ ካንሰር ከሚሞቱት 90 መቶ የሚሆነው በታዳጊ ሃገራት ላይ እንደሚገኙም ነው የተገለጸው፡፡

እድሜያቸው ከ20 አመት በፊት ሆነው የግብረስጋ ግንኙነት መጀመር፤ ኤችአይቪ ኤድስ በደማቸው ውስጥ መኖር ፤እና በአባላዘር በሽታ የተያዙ ሴቶች ለማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ተጋላጭ ናቸው።

ህመሙ ቀድሞ ከተደረሰበት መከላከል እንደሚቻልም ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በእሌኒ ግዛቸው

ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply