በኢትዮጵያ በየአመቱ 77 ሺ የሚሆኑ ሰዎች በካንሰር በሽታ ይያዛሉ ተባለ፡፡በሀገራችን የካንሰር ህሙማን ቁጥር እየጨመረ መሆኑን እና ካለፈው አመት በ10 ሺ ጭማሪ ማሳየቱን ጤና ሚኒስቴር አስ…

በኢትዮጵያ በየአመቱ 77 ሺ የሚሆኑ ሰዎች በካንሰር በሽታ ይያዛሉ ተባለ፡፡

በሀገራችን የካንሰር ህሙማን ቁጥር እየጨመረ መሆኑን እና ካለፈው አመት በ10 ሺ ጭማሪ ማሳየቱን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በጤና ሚኒስተር የካንሰር መከላከል እና መቆጣጠር አማካሪ ዶ/ር ኩኑዝ አብደላ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንተናገሩት የካንሰር ታማሚዎች መጨመር ብቻ ሳይሆን የሞት መጠኑም እየጨመረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አዲስ ከሚያዙ 77 ሺ የካንሰር ህሙማን 50 ሺ የሚሆኑት ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉም ብለዋል፡፡

በዋነኛነት እየተስፋፉ የሚገኙት የካንሰር አይነቶች የጡት ካንሰር፣የማህፀን በር ካንሰር እና የአንጀት ካንሰረ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የአኗኗር ዘይቤ መቀየር ፣ የአልኮል መጠጦች አብዝቶ መጠቀምና ሲጋራ ማጨስ ምክንያት መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ለካንሰር ህክምና አገልግሎት ላይ የሚውሉ ግብቶት እና የሚቀርቡ መድሃኒቶች በቂ አለመሆነናቸውንም አንስተዋል፡፡

አሁን ባለው ደረጃም የካንሰር ህክምና የተቋማት ስርጭት እና የተደራሽነት ደረጃ ዝቅ ያለ ነው ብለዋል፡፡

በአመት ከሚያዙት የካንሰር ህሙማን መጠን የህክምና አገልግሎቱን የሚያገኙት 15 በመቶ የሚሆኑት ብቻ መሆናቸውን ታውቋል፡፡

እንደ ጤና ሚኒስቴርም ችግሩን ለመቀነስ ግንዛቤ የመስጠት እና ተደራሽነትን የማስፋት ስራዎች በሰፊው እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ካንሰርን በሩቁ መፍራት ሳይሆን በሽታውን በደንብ ተረድቶ ማድረግ የሚቻሉ መፍትሄዎች ላይ መረባረብ ያስፈልጋል ሲሉ ዶ/ር ኩኑዝ አሳስበዋል ፡፡

ሐመረ ፍሬው

ሚያዚያ 11ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply