You are currently viewing በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ5ሺህ ሴቶች በማህጸን በር ካንሰር ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 10 ቀን 2014 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ በኢትዮ…

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ5ሺህ ሴቶች በማህጸን በር ካንሰር ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኢትዮ…

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ5ሺህ ሴቶች በማህጸን በር ካንሰር ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ7 ሺህ በላይ ሴቶች በማህጸን በር ካንሰር እንደሚያዙ እና 5ሺህ የሚሆኑት በዚሁ በሽታ ሳቢያ እንደሚሞቱ ተነግሯል። የጤና ጥበቃ ሚንስትር ድሬዳዋ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በተወያዩበት ወቅት የማህጸን ካንሰር ቀድሞ መከላከል እንደሚቻል ተነግሯል። የማህጸን በር ካንሰር ሴቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ለሞት ከሚያበቁ በሽታዎች ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በየዓመቱ 538 ሺህ የሚሆኑ ሴቶች በዚህ በሽታ የሚያዙ ሲሆን 275 ሺህ ያህሉ በዚሁ ሳቢያ በየዓመቱ ህይወታቸው ያልፋል። የማህጸን በር ካንሰር ወደ ካንሰርነት ከመቀየሩ በፊት ከ20 – 30 ዓመት ይወስዳል። በዚህ ጊዜ ታዲያ የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ በማድረግ ወደ ካንሰርነት ሳይቀየር በጊዜ በህክምና ማዳን ይቻላል። የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል በኢትዮጵያ እድሜያቸው 14 ዓመት ለሆናቸው ልጃገረዶች ክትባት መስጠት ከተጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። ዘንድሮም ከህዳር 27- 30 ክትባቱ እድሜያቸው 14 ለሆነ ልጃገረዶች ክትባቱን የሚሰጥ ይሆናል። ይህንኑ መነሻ በማድረግ በድሬዳዋ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን ማኅበረሰቡ የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባቱ የሚያስከትለው ጉዳት ባለመኖሩ እድሜያቸው 14 የሞላ ሴት ልጆቹን እንዲያስከትብ ጥሪ ቀርቧል ሲል አዲስ ዘይቤ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply