በኢትዮጵያ በግማሽ አመት ብቻ 1ሺህ 358 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው እንዳለፈ ተነገረ።

በ2016 አመት በባለፊት ስድስት ወራቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ምክንያት 1ሺህ 358 ዜጎች ለሞት መዳረጋቸው ተነግሯል።

በደረሱ አደጋዎች ምክንያትም ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን ንብረት እንደወደመ ነው የተገለጸው።

ባለፉት 6 ወራት ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ህግ የተላለፉ ተሽከርካሪዎችን በመቅጣት ከ 1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡

የመንገድ ደህንነትና መድህን ፍንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አባሶ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከልና ሕግ ተላልፈው የሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢውን የቅጣት ዕርምት ለመውስድ ቴክኖሎጅን በመጠቀም ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ሃላፊው አክለው እንደተናገሩት ከ 1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የመንገድ ደኀንነት ትምህርቶች በካሪኩለም ውስጥ ለማካተት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ እና የተሽከርካሪዎች ቴክኒክ ብቃት ማረጋገጫ ተቋማት ያልተገቡ ማስረጃዎችን እንደሚሰጡ የገለፁት ሥራ አስፈጻሚው ተገቢውን ክትትል በማድረግ ላይ እንገኛለ ብለዋል።

ለአደጋ አጋልጭ የሆኑ መንገዶች ተለይተው የማሻሻያ ሥራዎች መከናወናቸውና የሞተር አልባ ትራንስፖርትንም ለማስፋፋት በ13 ከተሞች የመንገድና መሰል መሰረተ ልማቶችን የማልማት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ተደጋጋሚ ጥፋት የሚያጠፉ አሽከርካሪዎች ላይ መንጃ ፈቃድ እስከመንጠቅ የሚያደርስ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የገለጹት ሃላፊው አገልግሎቱ በአዲስ አበባና ሸገር ከተሞች ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብአኤል
ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply