በኢትዮጵያ ባለፈዉ የፈረንጆች 2023 ዓመት ብቻ ከ50 በላይ ጋዜጠኞች መታሰራቸዉ ተገለፀ።በኢትዮጵያ የሚዲያ ነፃነቱና ሀሳብን በነፃነት መግለፅ በድጋሚ እየጠበበ መጥቷል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/vOEcUJeQT3InXVfZE8WvpqN15vLfiE94yPtv-1yKnMKmYSW3p_1fmWc6PSCgp_nSQHe3m9Eo9kF1ZHsz46jRpGzl6RLwjSvlZ1N8AGTmxxWhlUkkI-dvVagRjALnlPebtOa17b-K-zQZ3eMAcoIMW8DOEvU7VBUntr1OAxpVW-BOwEtDsiemBSmVxvZ3FjnbR509F18eAZVO_P-WWY1VpO0SroYN9TdW2NVrKwWksQfSUTGY_vNZfBAlInPlG0L9JgE4IYcJS86bUqx2RouoaIU4xs7DjS_AyEJwkbaV6_Fj3y0h3-XoipX2apjAC_4bCDOeIJxlb2vRcGD-4RCGJw.jpg

በኢትዮጵያ ባለፈዉ የፈረንጆች 2023 ዓመት ብቻ ከ50 በላይ ጋዜጠኞች መታሰራቸዉ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ የሚዲያ ነፃነቱና ሀሳብን በነፃነት መግለፅ በድጋሚ እየጠበበ መጥቷል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማህበር ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሀይለማርያም እንደተናገሩት “ሀሳብን በነፃነት መግለፅ እየተገደበ መጥቷል፣ ለዚህም ማሳየዉ በየግዜዉ እየታሰሩ የሚገኙት ጋዜጠኞችና ማህበራዊ አንቂዎች እንደ ምሳሌ መዉሰድ ይቻላል ብለዋል።

ጋዜጠኞቹ የህግ ጥሰት ፈፅመዉ ከሆነ በሀገሪቱ የህግ አግባብ ሊጠየቁ ይገባ ነበር፣ ነገር ግን በተቃራኒው ወደ ተለያዩ ራቅ ወዳሉ የሀገሪቱ ክፍል ተወስደዉ መታሰራቸዉን ተመልክተናል ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ዋነኛዉ ምክንያት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ነዉ የሚሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ አዋጁ መራዘሙ ደግሞ ጋዜጠኞቹ ፍትህ ሳያገኙ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ እየተሰቃዩ ይቆያሉ፣ ይህ ደግሞ በጣም አሳሳቢ ነዉ ሲሉ ገልፀዉታል።

በአማራ ክልል ታዉጆ የነበረዉና እንዳስፈላጊነቱ በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍል ይተገበራል የተባለዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት መራዘሙ ይታወሳል።

በአቤል ደጀኔ

ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply