በኢትዮጵያ ተጨማሪ 485 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸ

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 485 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7 ሺህ 45 የላቦራቶሪ ምርመራ 485 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 93 ሺህ 343 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 701 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 47 ሺህ 543 መድረሱንም አስታውቋል።

በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰአታት የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 426 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 44 ሺህ 372 ሰዎች መካከል 339 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 444 ሺህ 542 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

The post በኢትዮጵያ ተጨማሪ 485 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply