በኢትዮጵያ ተጨማሪ 510 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 958 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 510 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 958 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 5 ሺህ 839 የላብራቶሪ ምርመራ 510 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 98 ሺህ 391 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።
958 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 57 ሺህ 114 መድረሱም ተገልጿል።
ከዚህ ባለፈ የ5 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 508 መድረሱም ተመላክቷል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 510 ሺህ 144 ሰዎች ምርመራ መደረጉ ተገልጿል።
አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 39 ሺህ 767 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 346 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

The post በኢትዮጵያ ተጨማሪ 510 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 958 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply