በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት የፓተንት መብት ያገኙ የፈጠራ ዉጤቶች አስር ሺህ አይሞሉም ተባለ፡፡በአገራችን የፈጠራ ስራ ሰርተዉ የፓተንት መብት የተሰጣቸዉ ግኝቶች አስር ሺህ እንደማይሞሉ በባለ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/FLqFb_dAar69VhBi5fqS3o9S2i9Io36BvFTlPFQCQumaLUrjP1-meY7uNsmre7v9riInQJx2hS3p76Rj1aGOMXl0moBxmMByuSGPjTNAiI-g98ufOpkPTUar84q1ImDd6rOen6qL2CA2Zgqtas1Jp6INkvrzqfIHzDIoQyI9FaF7n0Ka0N1SliaaTJ-NmNlR2iluoVXQRBlKz52rEH39wta_LsUGDnE-XcgBT89wPY5tSqU_W8XSUtBG-tOMfb4Kazwua6aCwAABN3ChyEHFrXZIbh6DcOR60-EzAGqj2MnA-RR1gcvVYEb9n5N9X0SK1X3q1JyrXYCplalrhwJxlg.jpg

በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት የፓተንት መብት ያገኙ የፈጠራ ዉጤቶች አስር ሺህ አይሞሉም ተባለ፡፡

በአገራችን የፈጠራ ስራ ሰርተዉ የፓተንት መብት የተሰጣቸዉ ግኝቶች አስር ሺህ እንደማይሞሉ በባለስልጣኑ የፓተንት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ክፍል ሃላፊ አቶ ጌታቸዉ ጣፋ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

70 በመቶዉ ወጣት በሆነባት፣የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ባሉባት እና የህዝብ ቁጥሯ ከፍተኛ በሆነባት አገር ዉስጥ ቁጥሩ እጅግ አነስተኛ ነዉ ያሉት ሃላፊዉ ለወደፊት ግን የሚመዘገቡ ስራዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ነግረዉናል፡፡

የኢንዱስትሪያል ዲዛይን ወደ 3ሺ አከባቢ፣ በፓተንት 3መቶ እና ለአገልግሎት የቀረቡ ፈጠራዎች ደግሞ ወደ 4ሺህ አከባቢ መሆናቸዉን ነዉ የነገሩን፡፡

ሌሎች አገራት ይህን ቁጥር በሰዓት ዉስጥ የሚያስመዘግቡት ነዉ ያሉት አቶ ጌታቸዉ እነ ቻይና በዓመት ከ1.5 ሚሊየን በላይ አዳዲስ ፈጠራዎችን ያስመዘግባሉ ብለዋል፡፡

ሃላፊዉ መመዝገብ ያለባቸዉ የተሻሻሉ የእጽዋት ዝርያዎች መኖራቸዉን በማንሳት፤መዝጋቢዉ አካል ግብርና ሚኒስቴር ነዉ ያሉን ሲሆን እስካሁን ምዝገባ አለመጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከሶስት ወራት በፊት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስር በጤና እና በቴክኖሎጂ ወደ አራት የፈጠራ ስራዎች በፓተንት መመዝገባቸዉንም አቶ ጌታቸዉ ነግረዉናል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply