በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የዑለማ ም/ቤት የመፈንቅለ መጅሊስ ሙከራ ተድረጓል አለ

ባለፉት
ሳምንታት የተፈጠረው ችግርና አጀንዳ የመፈንቅለ መጅሊስ ሴራ ያለበት ነው ሲል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
የዑለማ ም/ቤት ገልፀዋል፡፡

በዚህም
ከዚህ በፊት ዑለማ ምክር ቤት የተጋዱና  በቀጥታ  ስራው ላይ የሌሉ የእምነቱ መሪዎች  የመፈንቅለ መጅሊስ ሴራ ያለበት  ስብሰባ በማካሄድ፤ በተግባርም ለመፈጸም ብሎም  በመግለጫ በማመላከት ህገ ወጥ ስራ ስረተዋል ሲል ነው የኢትዮጵያ
እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያስታወቀው፡፡

ይህንንም
ለመለየት የሚያስችል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ም/ቤት ልዩ ስብስባዉ አካሂዷል፡፡ ስብሰባዉ ልዩ
ነዉ የተባለዉ በፈጸመዉ የዲስፕሊን ግድፈት ምክንያት በዑለማ ምክርቤቱ ስራ አስፈጻሚ ዉሳኔ በታገዱ የቦርድ አባላት በህገ ወጥ
መንገድ ከተቋሙ በተወሰደዉ በመከነ ማህተምና ባለ አርማ ወረቀት በተደረገ ጥሪና በሌሎች ምክር ቤቱን ስርአት ጥሷል በተባሉ
ዝርዝር ምክንያቶች ናቸዉ ፡፡

የጠቅላላ
ጉባኤ ስብሰባ ለመጥራት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት አለመደረጉና ለጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ሊቀርብ፤ ሊነጋገርበት የሚችል አንዳች
ነገር የለም የሚል ነዉ፡፡ በዚህም ጠቅላይ ምክርቤቱ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪዉ ህገ ወጥ መሆኑን በመግለጽ እንዳይካሄድ መግለጫ
የሰጠበት በመሆኑ ተካሄደ የተባለዉ ጉባኤ ሕገ ወጥ ነዉ ሲል ወስኗል፡፡

 የመፈንቅለ መጅሊስ ሴራ ያለበት ስብሰባ ማካሄድ፤ በተግባርም ለመፈጸም በመግለጫ ማመላከት ህገወጥ ነዉ ሲል ጠቅላይ ምክርቤቱ አስታዉቋል፡፡ እንደ ዉሳኔም በህዝብ ዘንድ ጥያቄ ያስነሳዉንና ተቋሙን ያለ ፋይናንስ አቅም እርቃኑን ያስቀረዉን የ2011 የሐጅ አገልግሎት እንቅስቃስን በመመርመር መልስ ለመስጠት የተቋቋመዉን የልዩ ምርመራ ቡዱን ጸድቆ በዚህም በሚገኛዉ ዉጤት መሰረት እርምጃ እንዲወሰድ ተወስኗልም ተብለዋል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 30 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

Source: Link to the Post

Leave a Reply