በኢትዮጵያ እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች በንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ ተባለ። በኤድስ ሔልዝ ኬር ፍውንዴሽን (AHF) ኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ መ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/nr-s-qqOhyPPF4ZIT-Mktz4-t2Y4n48FZCT-orFW5_mvcfR_M9B2mF-KcR5sZ8KKvIi5UqUlJ9M8Si8Dr9SaTEdE9cpMhQD8Z60TELCcUZDbla96_jQnmYcdjor8cPjAEoThLajrERbEPANKC2DiT3nU9hcLpvHKyM2cD8PyGDI2n1sji56PqsdX-lfzGelbsM7wqykzfCURhLi6uR6x6WU-r-_2CWdyH1evMgaTofzIpfAPmPfgbwDOCZw5Cl1T-YHT4oMJMlnlO-U536u2xFJXPKMfSv3PH1KjJUyx694YKtVgcl8YW5ns1Poq-8tslc2UMXV1lvKcpMifFhxlNg.jpg

በኢትዮጵያ እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች በንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ ተባለ።

በኤድስ ሔልዝ ኬር ፍውንዴሽን (AHF) ኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ መከላከልና ምርመራ እንዲሁም በግንዛቤ አሰጣጥ የአፍሪካ ዩኒየን 13 ሀገራት ፕሮግራም ማናጀር አቶ ቶሎሳ ኦላና ፤ ከአራት ተማሪዎች አንድ ልጃገረድ ከትምህርት ገበታዋ ትሰናበታለች ብለዋል።

አቶ ቶሎሳ ይህን ያሉት በዛሬው እለት በተስፋ ብረሃን ሀይስኩል ትምህርት ቤት ፤አለማቀፍ የወር አበባ ቀን እየተከበረበት ባለበት ወቅት ነው።

የኤድስ ሔልዝ ኬር ፍውንዴሽን (AHF) ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ዶከተር መንግስቱ ገ/ሚካኤል በክብረ በአሉ ላይ እደገለፁት ፤የዘንድሮ የወር አበባ ቀን የሚከበረው” ለወር አበባ ምቹ የሆነ አከባቢ እንዲኖረን በጋራ እንረባረብ”በሚል መሪቃል ነው።

የወር አበባ ቀን እየተከበረ የሚገኘው በሃገራች ለስምንተኛ ጊዜ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ11ኛ ጊዜ ነው።

በንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ምክነያት ከትምህርት ገበታቸው ሴትተማሪዎች እንዳይቀሩ ለማድረግ የንፅህና መጠበቂያ ሞዴና የግንዛቤ ማስጨበጫ ምክር ድግፍ አድርጓል።

ኤድስ ሔልዝ ኬር ፍውንዴሽን (AHF) ኢትዮጵያ ፤አለም አቀፍ ለትርፍ ያልተቋቋመ ግብረሰናይ ድርጅት ነው ተብሏል ።

ልዑል ወልዴ

ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply