You are currently viewing በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊያን ጉሮሮ ላይ የቆመው ሁሉ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊያን ቆሜያለሁ ማለት አይችልም፤ ቢልም እውነትን በሚፈልጉ፣ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም!  ጥቅምት…

በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊያን ጉሮሮ ላይ የቆመው ሁሉ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊያን ቆሜያለሁ ማለት አይችልም፤ ቢልም እውነትን በሚፈልጉ፣ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም! ጥቅምት…

በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊያን ጉሮሮ ላይ የቆመው ሁሉ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊያን ቆሜያለሁ ማለት አይችልም፤ ቢልም እውነትን በሚፈልጉ፣ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም! ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር “ለኢትዮጵያ መቆም!” በእጅጉ የሚደገፍ እና የሚበረታታ ነገር ነው! ቀደምት ጀግኖቻችን በቅብብሎሽ ያሳዩንና ያወረሱን መገለጫችንም ይህ ነው። ኢትዮጵያ ተነካች ሲባል ዜጎቿ ሁሉ ነው የሚነኩት። በተባበረ ክንድ አስተማሪ የጀግና ምላሽም ነው የሚሰጡት። በዚህ መልኩ ነው ኢትዮጵያ የቅኝ ገዥዎችን ወረራ ቀልብሳ ድባቅ በመምታት እና አሳፍራ በመመለስ፣ ምስጋና ይግባቸውና ቀደምት አርበኞቻችን በከፈሉት የደም እና የአጥንት ክቡር መስዋዕትነት የጥቁር ህዝብ ኩራት ሆና ክብሯ በሰንደቋ ብዙዎች በማይደርሱበት ከፍ ባለ ማማ ላይ ተሰቅላ የኖረችው። በመሰረቱ አሁን ላይ አስቸጋሪ እና አሳዛኝ የሆነው ግን እንደ መልካም ነገር በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊያን ጉሮሮ ላይ መቆምን ስርዓታዊ መገለጫ ማድረጋችን ነው! እንደ ተቀጥላ፣ አልሸሹም ዞር አሉ ስርዓት፣ እንደ መንግስት በእውኑ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊያን ነው የቆምነው? ወይስ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊያን ጉሮሮ ላይ ነው የቆምነው? ለማን እንደቆምን በህዝብ ዘንድ የሚታወቅ መሬት ላይ ያለ እውነታ ነው። ለብዙዎቻችን ያስቸገረው ከልብ ያልሆነውን ለመሆን በአስመሳይነት ለማሳዬት መጣራችን ነው! ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሆነው ማንነታችን ጎልቶ እየወጣብን መቸገራችን ነው! ከልብ የሆኑትን የሚሆኑ ብዙዎች እንዳሉም አይዘነጋም! በርካቶቻችን በአንደኛው ቁስል ሌላውን ለመፈወስ በደካማ የዘር እና የጎጥ እሳቤያችን ውስጥ ተመርዘን አጉል መዳከሩን እንደቀጠልንበት ነው! ከማናቸውም የተበደሉ ንጹሃን ጎን መቆምም ሰዋዊነት ነው! አሁንም ችግሩ ነገን፣ ከራሳችን ውጭ ሌላውን እና በሌላው ቦታ ሆነን ሌላውን ለማዬት ብዙ እየፈቀድን አለመሆናችን ነው! ይህ እርስ በርስ የመጠላለፍ እና የመጠቃቀም የእሳቤ አዙሪት እንዲቀር እስካልሰራንበት እና በአስተሳሰብ እስካልታከምን ድረስ ቶሎ የሚፋታን በሽታ አይደለም! አዎ ያስቸገረው “ቅብነት”፣ አስመሳይነትና አደርባይነት ነው! ያልሆኑትን ለመሆን አጉል መንፈራገጥ ነው! ቀደምት ጀግኖቻችን የውጭ ወራሪን በመርዝ ጋዝ ጭምር የፈጸመባትን አውሬያዊ ጭካኔ ተቋቁማ ያለምንም ተስፋ መቁረጥ ፣ ከጀግኖች አርበኞች ጋር ልጆቿን አሰልፋ በጽናት የውስጥ የሆድ አሽከርን፣ አድርባይን፣ ከሃዲን እና ባንዳን ጭምር ታግላ ያሳፈረች፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ቀይ ሰንደቋን ከአለም አደባባይ ከፍ አድርጋ በኩራት ያውለበለበች ገናና ታሪክ ያላት ውዷ ሀገሬ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናት! ኢትዮጵያ ሀቀኛ አንድነቷን ስታበረታታ፣ መልካም እሴቶቿን ስታከብር፣ ባንዳዎችን፣አጉል አስመሳዮችን፣ ቅቦችን፣ ነገን ለማሰብ ትንሽ ጊዜ እንኳ የሌላቸውን፣ በቆሸሸ የደካሞች የፖለቲካ ሴራ የተነሳ ሀሰት ትርክትና በጥላቻ ህሊናቸው የታወሩ አካላትን አውሬያዊ ድርጊት፣ ጅምላ ጨፍጫፊዎችን፣ሀገር እና ወገን ዘራፊዎችን ስትጠየፍ ብቻ ሳይሆን አምርራ ስትታገል ያን ጊዜ እውነቷ ጎልቶ እና ደምቆ አፍ አውጥቶ ይናገራል። ኢትዮጵያዊነት የአንደኛው ቁስል የእኔም ቁስል ነው፤ ህመሙ ህመሜ ነው፤ አንድ ጣቱ የተቆረጠ፣ የቆሰለ ወይም የደማ ሰው ሙሉ አካሉ ጤነኛ እንደማይሆነው ሁሉ፣ የጣቱ ህመም መላ ሰውነቱን ዘልቆ እንደሚሰማው ሁሉ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በማንነታቸው ብቻ የዘር ፍጅት ሰለባ እየሆኑ ላሉ በዋናነት አማራዎች እና ሌሎች ጥቃት ለደረሰባቸው እና ለሚደርስባቸው ኢትዮጵያዊ ወገኖች ሁሉ ሰዋዊ ውግንናን አለመንፈግን፣ ብሎም ለምን ብሎ መጠየቅንና መታገልን፣ ድምጽ ማሰማትን ይጠይቃል። ለኢትዮጵያ መቆም፣ ለኢትዮጵያ ድምጽ ማሰማት እልቂትን፣የዘር ፍጅትንና ርሃብን መደበቅ እና ለምን ተብለው ሲጠየቁ “ሀገር ሊያፈርሱ መጡ፤ ተነስ እንሰለፍ” እያሉ የራስን ገመና እና ወንጀልን ደጋፊ ህዝብን እንደ ምሽግ በመጠቀም መደበቅ ሳይሆን ለእውነተኛ ሰብአዊነት መቆምን፣ ለሀቀኛ አብሮነት እና ወንድማማችነት በርትቶ መስራትን ይጠይቃል! ስልጣንም ሆነ ባለስልጣን፣ ስርዓትም ሆነ መንግስት ጊዜያዊ ነው፤ ኃላፊ ጠፊ ነውና ሁሉንም ነገር ከስልጣነ መንበር ጋር ብቻ አለማያያዝንም ይጠይቃል! በእርግጥም በጣም የቸገረው መከራን መልመድ እና ያለንን እምቅ አቅም አውቆ ለስር ነቀል ለውጥ አለመስራታችን እና የስርዓት ጥገኛ ለመሆን፣ ከሀገር እና ወገን ይልቅ ስለ ስርዓት ሲባል መሬት ላይ ያለን እውነታ ለመድፈቅ መተባበራችን ነው፤ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ በሄደበት ለመሄድ ገደልም ቢሆን መፍቀዳችን ነው። መቀጠል ስላለባት፣ በትውልድ ቅብብሎሽ አያሌ መስዋዕትነት ስለተከፈለባት ኢትዮጵያ መቆምም ሆነ ድምጽ መሆን፣ ማናቸውንም ያልተገቡ ጣልቃ ገብነቶችን በሰለጠነ መልኩ መቃወም በራሱ ችግር አይደለም! ስለ ኢትዮጵያ መቆም እና ድምጽ ማሰማት ስለ ሀገር እና ስለ ወገን አንድነት እና ዘላቂነት የጠራ አመለካከት መያዝ ቀዳሚው ሆኖ ሀገርን ከቅኝ ገዥዎች በባሰ አለማጎሳቆልን ፣ በቋንቋ እና በጎሳ የተከፋፈለን በታኝ የሆነውን (አንቀጽ 39) የወያኔንና የኦነግን ህገ መንግስት የሙጥኝ ብሎ አለማምለንክን ሊጨምር ይገባል። በተጨማሪም ኢትዮጵያዊነት የተከፋፈለ፣ ጥገኝነትን የለመደ፣ በግጭት እና በንጹሃን ደም መፍሰስ የሚነግድ፣ ከጎሳ አጥሩ ላለመውጣት የወሰነ ወይም አቅም ያጠረው፣ በጥቅም የተሸበበ እና የታወረ፣ ለሀገሩ ዜጋ፣ሉአላዊነት፣ወግ፣ባህል፣እምነት፣ እሴትና አስተሳሰብ ክብር የሌለው፣ ነገን አርቆ ለማዬት ያልፈቀደ፣ ጸረ ለውጥ የሆነን፣ የተንሸዋረረ እይታን ገንዘቡ ያደረገን፣ የህዝብ ሳይሆን የስርዓት አገልጋይ የሆነን ካድሪን ከራስ ጀምሮ ማስተካከልን አብዝቶ ይጠይቃል። ስለ ኢትዮጵያ መቆምም ሆነ ድምጽ ማሰማት እንደ አብነትም ላለፉት አራት ዓመታት የዘር ፍጅት ሰለባ የሆኑ አማራዎችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪነት ከጥፋት ተባባሪነት፣ በሴረኞች ከጋትነው እኛንም ጨምሮ ከሚገድለን መርዝ፣ እንደ ሰው ፈርሰን ከተሰራንበት ጭፍን ጥላቻ እና የሀሰት ትርክት በመላቀቅ ስርዓታዊ እና መንግስታዊ ኃላፊነትን በመወጣት መታደግ ሲገባ ወደ አደባባይ ወጥተው “ሞት በቃን!” ብለው እንኳ ድምጻቸውን እንዳያሰሙ አዘውትሮ ከመከልከል አምባገነናዊ እና አፋኝ አካሄድ መላቀቅን ይጠይቀናል። ይህ ብቻ አይደለም። የመብት ጠያቂዎችንና የንጹሃን ድምጾችን ከማዋከብ፣ ከማሰር እና ከማፈን እንዲሁም የህዝብ ጭሆትንና ለቅሶን ካለመስማት፣ ተጠያቂነትን ካለማስፈን፣ ወንጀልን በስሙ ካለ መጥራት፣ከድብብቆሹ መንገድ ካለመውጣት፣ በገፍ እና በግፍ ከሚራቡት፣ ከሚጨፈጨፉት፣ከሚታረዱት ከታጋቾች እና መንገድ ተዘግቶ በከበባ ውስጥ ካሉት ንጹሃን ዜጎች ጎን ካለመቆም ሾተላይ መላቀቅን፣ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ጎን ካለመቆም ጎታች እና እርጉም ከሆነ ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ አካሄድ ራስን ማላቀቅም አስፈላጊ እና የግዴታ ያደርገዋል። ከአሸባሪዎችና ለብአዳን ካደሩ ከውስጥ ወራሪዎች እና አራጆች ጋር በስንቅም፣በትጥቅም፣በመረጃም ሆነ በሌላ ማናቸውም መንገድ አለመተባበር ብቻ ሳይሆን አምርሮ መታገልም መሰረታዊ ነገር ነው። የዘር ማጥፋት ወንጀል ከባድ ነው! የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ ስርዓታዊ እና መንግስታዊ ከባድ ተጠያቂነትን ማስከተሉም አይቀርም! ስለ ኢትዮጵያ መጨነቅ ካለ እኮ ሱዳን ያለታሪካችን በኃይል ገብታ በጎንደር በኩል የያዘችውን ሰፊ ለም መሬትን ማስመለስም ቀዳሚ የሉአላዊነትን ጉዳይ መሆኑም መታወቅ አለበት። አውሮፓውያንም ሆኑ ምዕራባዊያን፣ ሌሎች የውጭ ሀገራት ከራሳቸው ጥቅም አንጻር ተነስተው ለአንዱ አካል የውግንና አቋም እንደሚወስዱ እና አሻንጉሊት እንደሚፈልጉ እና እንደሚያደርጉም ይታወቃል። አሁንን ጨምሮ ባለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የዘር ፍጅት ሲፈጸም ዴንታ አልነበራቸውም፤ አይኖራቸውምም፤ የረከሰ ፖለቲካቸውን ነው የሚያዩት። ከራሳቸው ሀገር በተለዬ መልኩ ለሌሎች ቅብ እና አስመሳይ ሆነው ስለሚቀርቡ ስር ነቀል ለውጥ እንዲመጣ ሳይሆን ሀብት ለመዝረፍ የእነሱ ታዛዥ የሆኑ ቅቦችን ነው የሚፈልጓቸው። ብዙውን ጊዜ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የጦር መሳሪያቸውን እየነገዱ፣ እርስ በርስ እያጨፋጨፉ ይቀጥላሉ። ሰብአዊነትን ጨምሮ ሁሉንም ከእውነት አንጻር ሳይሆን ከሀገራቸው ጥቅም አኳያ ብቻ ነው የሚያዩት። ለዚህ ሁሉ ግን ዋናው መድኃኒቱ ወደ ህዝብ መጠጋት ብቻ አይደለም፤ ህዝብን ማዳመጥ እና የህዝብን ችግር ለመፍታት መወሰንና አምርሮ መታገል ነው! ህዝብን፣ለውጥንና እውነትን መቅረብ እና መቀበል እንጅ አለመፍራት ነው፤ ሰላም፣ መከባበርንና አንድነት አብሮ የመኖር ተፈጥሮአዊ ቁልፍ መሆኑን ተገንዝቦ፣ ከዘራፊነት፣ከገፊነት፣ ከጨፍላቂነት፣ ከአሳዳጅነት፣ከተበላሸው የመጠላለፍ ማካቬሊያዊ የሴራ ፖለቲካ፣ ከዘረኝነት አጥር፣ ከረጢት እና ጉድጓድ ወጣ ብሎ ለማሰብ እና ለመስራት መዘጋጀት እንዲሁም የሀገርንና የወገንን ጥቅም ማስቀደም ነው ፍቱን መድኃኒቱ! ከምንም በላይ ግን ከሰልፍም ሆነ ከሰይፍ በበለጠ ዘመኑ አብዝቶ የሚጠይቀውን የዲፕሎማሲ አቅምን አጠንክሮ ብቁ የታላቋ ሀገር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ጠበቃ፣ ታጋይ ሆኖ መገኘት ነው! እንዲህ እያደርግን ለኢትዮጵያ በምንቆም፣ ድምጽ በምንሆን ጊዜ በእጅጉ ያምርብናል! ጠላቶቻችንም ይፈሩናል፤ አክብረው ይወዱናል! ዘገባው የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ነው ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply