በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ላሉ የጸጥታ ችግሮች የስልጣን ፍላጎት፣ የተዛቡ ትርክቶች ዋነኛ ምክንያቱች ናቸው አለ የሰላም ሚንስቴር የሰላም ሚንስቴር የ2016 በጀት ዓመት የሶስት ወራት እቅድ አፈጻ…

በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ላሉ የጸጥታ ችግሮች የስልጣን ፍላጎት፣ የተዛቡ ትርክቶች ዋነኛ ምክንያቱች ናቸው አለ የሰላም ሚንስቴር

የሰላም ሚንስቴር የ2016 በጀት ዓመት የሶስት ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል።

ሚንስቴሩ ለምክር ቤቱ አባላት ባቀረበው ሪፖርት ላይ እንደገለጸው አሁን ላይ በኢትዮጵያ ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ደርሷል ብሏል።

ተፈናቃዮቹን ወደ ቀድሞ ቤታቸው ለመመለስ እንደ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም ) ካሉ ሌሎችም ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንም ሚንስቴሩ አስታውቋል።

የሰላም ሚንስቴር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደዓ በሰጡት ምላሽ በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ላሉ የጸጥታ ችግሮች የስልጣን ፍላጎት፣ የተዛቡ ትርክቶች፣ ስለ ሀገር ያለው አመለካከት የተዛባ መሆን ዋነኞቹ ምክንያቶች እንደሆኑ ተናግረዋል።

አቶ ታዬ አክለውም በኢትዮጵያ የጎሳ እና ብሄር ግጭቶች መቀነሳቸው፣ አሁን ላይ ያሉ የጸጥታ ችግሮች በብሄር እና ጎሳ መካከል ያሉ እንዳልሆኑም በምላሻቸው ላይ ገልጸዋል።

ይሁንና ሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉት የጸጥታ ችግሮች ያቀዳቸውን ስራዎች ለመፈጸም እንቅፋት እንደሆኑበት ገልጿል።

ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply