
“በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ላይ የሚፈጸመው መንግስታዊ ጄኖሳይድ ይቁም!” ሞዐ ተዋህዶ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ እነዚህ ሰባቱ የኦርቶዶክሳዊያን ቀዳሚ ጥያቄዎች እንዲመለሱ አሁንም አጥብቀን እንጠይቃለን። (1) በሕገመንግሥት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና መሰል መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለጥቃት የሚያጋልጡ መልዕክቶች በአስቸኳይ በሕግ እንዲታገዱ ፣ (2) ኦርቶዶክሳዊያንን ለይቶ ከሥራ፣ ከመንግሥት ኃላፊነት፣ ከሀብት ማፍራት እድሎች የሚያገል ከቀበሌ እስከ ፌደራል የተዘረጋው ሃይማኖታዊ መንግሥትና መዋቅር በአስቸኳይ እንዲቆምና ሃይማኖታዊ ሳይሆን ሕዝባዊ መሆኑን በተግባር እንዲያረጋግጥ፣ (3) ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን በቋንቋና በተለያዩ ዘውጎች ለመከፋፈል የሚደረገው ፖለቲካዊ ጥረት በጥናትና በምርምር ስም የሚደረጉ የመከፋፈል ዘመቻዎች እና ተግባራት እንዲታገዱ፣ (4) በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠሩ የአካል፣ የሥነልቦና፣ የኢኮኖሚ፣ የማኀበራዊ፣ የፖለቲካ፣ የማፈናቀል፣ ከአገራዊ ተሳትፎ የማግለልና የፍጅት ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ (5) እስከ አሁን የተፈጸሙ ጥቃቶች በዝርዝር ተገልጾ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እና የተጎዱት እንዲካሱ፣ (6) በመላው አገሪቱ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳዊያን ወደ ቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ፣ (7) “አዲሲቷ ኢትዮጵያ” በሚል ሽፋን ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የማጥፋት ፖለቲካዊ ሂደት በአስቸኳይ እንዲገታ እና በግልጽ ይቅርታ ተጠይቆ እርምት እንዲወሰድ፣ ምንጭ_Moa_Tewahido (ሞዐ ተዋህዶ)
Source: Link to the Post