በኢትዮጵያ ከፍተኛ የደም መጠን የሚሰበስበው ከተማሪዎች መሆኑ ተገለጸ።

በሀገሪቱ በየአመቱ ከሚሰበሰበው አጠቃላይ የደም መጠን ከፍተኛ መጠን የሚገኘው ከተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጲያ የደምና ህብረ ህዋስ ባንክ በየአመቱ ከሚሰበስበው የደም መጠን 35 በመቶ ያህሉን የምሰበስበው በትምህርት ተቋማት ነው ብሏል።

ቀሪው የደም መጠን የሚሰበሰበው በተለያዩ ጊዜያት በሚዘጋጁ ንቅናቄዎችና ዘመቻዎች እና በቋሚነት ደም ከሚለግሱ ዜጎች ነው ተብሏል።

ከሌላው ማህበረሰብ በተሻለ ተማሪዎች ደም የመለገስ ፍላጎታቸው ከፍተኛ ነውም ብሏል።

የኢትዮጲያ የደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በኢትዮጵያ በቋሚነት ደም ከሚለግሱ ዜጎች ውጪ በፍላጎት ደም የሚለግሱ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ ነው ብለዋል።

ይህ ሁኔታ በአዲስ አበባም ሆነ በክልሎች ተመሳሳይ እንደሆነም ገልጸዋል።

ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ያሉ ተማሪዎች በተለያየ ጊዜ ደም የመለገስ ባህል እንዳላቸው የተናገሩት አቶ ሐብታሙ ይህ ባህል ሌላው ማህበረሰብም ሊያዳብረው ይገባል ብለዋል።

ሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply