በኢትዮጵያ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ ወረርሽኝ መያዛቸው ተነገረ

ሊጠናቀቅ ወራቶች በቀሩት የ2016 በጀት አመት ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎች በወባ ወረርሽኝ መያዛቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በቂ ሀብት እንደሚያስፈልግ ያነሱት የጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሕይወት ሰለሞን በአመቱ 19.7 ሚሊዮን አጎበር ወደ ሀገር መግባቱንም ተናግረዋል።

እንዲሁም የትንኝ ቁጥጥር ስራ ና የመኝታ አጎበሮችን ተደራሽ የማድረግ ስራዎች እንደሚሰሩ አንስተዋል።

በሀገሪቱ ድንበር ላይ ያሉ ግንኙነቶችንም ወረርሽኙን ከመከላከል አኳያ ጥንቃቄ ሊኖርው እንደሚገባ ገልፀዋል ።

የወባ ወረርሽኝ ሁለት አይነት ወቅቶች ሲኖሩት አንዱ የበልግ ሰዓት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የክረምት መግቢያ ነው።

75 በመቶ የሚሆኑት የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወባማ ሲሆኑ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ህዝብ ደግሞ 69 በመቶ የሚሆነው በዚሁ አካባቢ እንደሚኖሩ ተነስቷል።

ሀመረ ፍሬዉ

ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply