በኢትዮጵያ ከ77 ሺ የሚጠጋ የካንሠር ህሙማን 12 ሺ ያህሉ ብቻ ሕክምናውን እንደሚያገኙ ተገለፀ።በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሚመዘገበው 77 ሺህ የሚጠጋ የካንሠር ህሙማን 12 ሺህ ያህሉ ብቻ ሕክም…

በኢትዮጵያ ከ77 ሺ የሚጠጋ የካንሠር ህሙማን 12 ሺ ያህሉ ብቻ ሕክምናውን እንደሚያገኙ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሚመዘገበው 77 ሺህ የሚጠጋ የካንሠር ህሙማን 12 ሺህ ያህሉ ብቻ ሕክምናውን እንደሚያገኙ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ወደ ሕክምና ከሚመጡት 75 በመቶዎቹ ህመሙ ውስብስብ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ የሚመጡ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ይህም የታማሚውን ታክሞ የመዳን ዕድል በመቀነስና ሕክምናውንም የበለጠ ውድ የሚያደርገው መሆኑ ተገልጿል።

የመሠረተ ልማትና የማኅበረሰቡ የግንዛቤ እጥረት፣ በሚፈለገው ልክ የሕክምና ባለሙያ አለመኖር፣ ለሕክምናው የሚውሉ ዕቃዎች ከውጭ ሀገር የሚገቡ መሆናቸውና ለግዥ ረዥም ጊዜ መውሰዱ፣ ብልሽት ሲያጋጥምም መለዋወጫ በቀላሉ አለመገኘቱ የሕክምናውን ተደራሽነት ውስን ማድረጋቸው ተመላክቷል።

ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply