በኢትዮጵያ የሚገኙ የሰባት አገራት ኢምባሲዎች የትግራይን ግዛቶች “አወዛጋቢ ቦታዎች” በሚል ቃል መግለጣቸውን የትግራዩ ተቃዋሚ ሳልሳዊ ወያነ ኮንኗል።

ፖርቲው፣ “አወዛጋቢ” የተባሉት አካባቢዎች “በኃይል የተያዙ የትግራይ ግዛቶች እንጅ ውዝግብ የተነሳባቸው አይደሉም” ብሏል።

ኤምባሲዎቹ የትግራይ ግዛቶችን በኃይል የያዙ ኃይሎች በመውጣታቸው አስፈላጊነት ላይ አጽንዖት እንዲያደርጉ ፓርቲው ጠይቋል።

የአሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያንና ጃፓን ኢምባሲዎች፣ በሰሜን ኢትዮጵያ “ውዝግብ ባለባቸው አካባቢዎች” የተፈጠረው አዲስ ውጥረት እንዳሳሰባቸው ቅዳሜ’ለት ባወጡት መግለጫ መግለጣቸው አይዘነጋም።

ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply