በኢትዮጵያ የሚገኙ የቢዝነስ ተቋማትን ለመደገፍ የአዉሮፓ ህብረት 2.2 ቢሊየን ብር ድጋፍ ሊያደርግ ነዉ፡፡የኢኮኖሚ መልሶ ማቋቋም ድጋፍ ለማድረግ የአዉሮፓ ህብረት ከጀርመን እና ኔዘርላንድ ጋ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/eYmAn2pUEelGRnMyp5VVuYS7R-Bb_kYDyucsYP7EUcxnChHRERSAingdBqiwQ4DhqxEoPSDYKQyBmx4EFPsL_TSk9-Kh0lWLwNaQ_7Yeq1SdYJX0CHxfrnNjASdvIkfQXK7GBjefPcrqEMtK6p9CsWjb49Pqk4ZW7XayDrLKm9GyoRDjE2FNLEzdZcIM5rJTrVjQZoPC1U-9lXh-jyI1fgE7EbW7XOr0wXN4bVFK0IYNMq-1mOEH8w0sL3paub2XABCz9MnEBGiZobMbJMITFUBz7v2lHd7e7wXKpmFkD9hrTLMDDx6ODQ8Zv2ENU9Zfu-mC_wm21-S0nUycrFDkXQ.jpg

በኢትዮጵያ የሚገኙ የቢዝነስ ተቋማትን ለመደገፍ የአዉሮፓ ህብረት 2.2 ቢሊየን ብር ድጋፍ ሊያደርግ ነዉ፡፡

የኢኮኖሚ መልሶ ማቋቋም ድጋፍ ለማድረግ የአዉሮፓ ህብረት ከጀርመን እና ኔዘርላንድ ጋር በመሆን አዲስ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል፡፡

ፕሮግራሙ በሶስቱ ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ለአራት ዓመታት የሚቆይ ነዉም ተብሏል፡፡

በአዉሮፓ ህብረት እና አጋሮቹ የሚተገበረዉ ፕሮጀክቱ የአገር ዉስጥ ኢኮኖሚን በማሳደግ በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ጉዳት የደረሰባቸዉን የማይክሮ፣ ጥቃቅን እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በዘላቂነት የማስቀጠል ሀሳብ እንዳለዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

በተለይም በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ያሉ ኢንተርፕራይዞችን ለመደግፍ በዕቅድ መያዙ ተገልጿል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply