በኢትዮጵያ የሚጥል በሽታን ለማከም የሚረዱ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት አጋጥሟል ተባለ በኬር ኢፕለፕሲ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አብይ አስራት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት የህክምና…

በኢትዮጵያ የሚጥል በሽታን ለማከም የሚረዱ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት አጋጥሟል ተባለ

በኬር ኢፕለፕሲ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አብይ አስራት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት የህክምና ማሽኖች እጥረት መኖሩ የህክምናው ተደራሽነት አናሳ እንዲሆን  አድርጓል ።

የሚጥል ህመም ላይ ተሰማርደተው የሚሰሩ የኒውሮሎጂስቶች ቁጥርም ከ 70 እንደማይበልጡ ተናግረዋል፡

ካሉት 70 ባለሙያዎች ውስጥም ሁሉም  ስራ ላይ ናቸው ማለት እንደማይቻል እና ከነዚህም አብዛኞች በአዲስ አበባ ላይ እንደሚገኙ ሰምተናል ፡፡

በዚህም ምክንያት የባለሙያ እጥረቱ በሰፊው ይስተዋላልም ብለዋል፡፡

እንደ አለም ጤና ድርጅት መረጃም በኢትዮጵያ ውስጥ ከ 1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች  የዚህ መሽታ ተጠቂ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡

ከነዚህም ውስጥ ህክምናውን የማግኘት እድል ያላቸው 5 ፐርሰንቱ ብቻ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

ኬር ኢፕለፕሲ ኢትዮጵያ ከተቋቋመ  9 አመት የሞላው ሲሆን  የሚጥል ህመም ያለባቸው ታማሚዎች እንደማንኛውም ሰው መገለል ሳይደርስባቸው የሚኖሩበት መንገድ ለማመቻቸት አለማ ያደረገ ነው ተብሏል ።

የድርጅቱ መሰራችም የዚህ ህመም ተጠቂ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

የሚጥል ህመም ያለባቸውን ሰዎች ተሻለ ህክምና  እንዲያገኙ እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማረግ ስራዎችን ይሰራል ብለዋል፡፡

በማበረሰቡ ዘንድ በእርግማን ነው የሚመጣው የሚል እሳቤዎች መኖራቸው ብዙዎች ወደህክምና ተቋም ሄዶ እንዳይታዩ መንስኤ መሆናቸውን አቶ አብይ ተናግረዋል ፡፡

በሀገራችን ያሉት የሚጥል በሽታ መድሀኒኖች ውስን እንደሆኑ  እና ዋጋቸውም ውድ በመሆኑ ታማሚው ላይ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር አንስተዋል፡፡

ያለውን ጫና ለመቀነስም መድሃኒቶቹ በነፃ ገብተው የሚሰጥበትን መንገድ የሚመለከተው አካል ቢያመቻች የተሻለ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ኬር ኢፕሊፕሲ ኢትዮጵያ” ድርጅትም ቋሚ የሚረዳው አካል ባለመኖሩ ሁሉም ማህበረሰብ ለዚህ ትኩረት ሰቶ ባለው አቅም ድጋፍ ቢያደርግ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ሲሉ አቶ አብይ ጠይቀዋል ፡፡

ሀመረ ፍሬው
መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply