በኢትዮጵያ የማይሰጡ የአይን ህክምናዎችን መስጠቷን እስራኤል አስታወቀች::

የእስራኤል መንግስት በኢትዮጵያ ሊሰጡ የማይችሉ የአይን ህክምና አይነቶችን ባለሙዎችን በመላክ መስጠቷን በኢትዮጵያ የሀገሪቱ ኢምባሲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት፤16 አባላትን የያዘ የህክምና ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የአይን ህክምና እየሰጠ ነዉ ብለዋል፡፡

የህክምና ቡድኑ በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ለ 250 ዜጎች የአይን ሀክምና እንደሰጠም አምባሳደሩ ነግረዉናል፡፡
በትናትናዉ ዕለትም በፕሮፌሰር ሞሪስ ሆስቲን የተመራዉ ቡድን በምንሊክ ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና ሰጥቷል፡፡

የህክምና ቡድኑ ለ 1ሺህ 4 መቶ በላይ የአይን ህሙማን ምርመራ ማድረጉን የገለፁት አምባሳደር አለልኝ፤ በቀጣይም እነዚህን ዜጎች ለማከም ተመልሶ ይመጣል ብለዋል፡፡

የልብ ህሙማን ህጻናትም ወደ እስራኤል ሀገር በመዉሰድ ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ነዉ ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የእስራኤል መንግስት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉንም አምባሳደሩ ገልፀዋል፡፡
እስራኤል የህክምና ባለሙያዎችን ማሰልጠኗን የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥልም ታዉቋል፡፡

ይሁን እንጅ የህክምና ቁሳቁሶቹ በተፈለገዉ ጊዜ ለህሙማን እንዳይደርሱ የኢትዮጵያ ጉሙሩክ አሰራር እንቅፋት እየሆነ ስለሆነ ይህ ችግር መፈታት አለበት ነዉ ያሉት አምባሳደሩ፡፡
የእስራኤልና የኢትዮጵያ ታሪካዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አምባሳደሩ እኛ ድጋፍ ስናደርግ የኢትዮጵያ መንግስት በጎ ነገርን መደገፍ አለበት ብለዋል፡፡

በአባቱ መረቀ
የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply