- የብልፅግና ፓርቲና የብልፅግና ቤተክርስቲያን ምስል
የብልፅግና ቤተክርስቲያን ምስል ቢጫ፣ሰማያዊና ቀይ ሰዎች እጃቸውን ወደ ላይ ዘርግተው የሚዘሉ ሰዎች አናት ላይ መስቀል ከነ ፈነጠቀው ጸዳሉ ይስተዋላል፡፡ በአንፃሩ የብልፅግና ፓርቲና ሁለት እጆች ተዘርግተው ሰማያዊ፣ ቢጫና ቀይ ሰዎች በሰማየ ሰማያቱ ላይ የፈነጠቀውን የፀሐይ ብርሃን አይተው ሲጨፍሩ ይስተዋላል፡፡ የሁለቱም ቀለማቶች አንድ ዓይነት መሆናቸው ሰማያዊ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት መሆናቸውና ሦስት እጃቸውን ወደላይ አድርገው የሚዘሉ ሰዎች መሆናቸው ዝም ብሎ ገጠመኝ ሊሆን አይችልም እንላለን፡፡ የብልፅግና ቤተክርስቲያን የተጀመረው በአስራ ዘጠነኛው ክፍለዘመን የአዲስ ሃሳብ አፋላቂዎች ንቅናቄ ሲሆን በ1950 እኤአ በሃገረ አሜሪካ በመዳን ቅሪቶች ዘመን የብልፅግና ቤተክርስቲያን ነገረ መለኮት ተጀመረ፡፡ (www.Prosperity church logo)1 ድረ-ገፅ አይተው ትዝብትዎን ያጋሩ፡፡
- የብልፅግና ፓርቲና ልዩ ልዩ የኃይማኖት እምነት ተቆማት
የብልጽግና መንፈሳዊ ትምህርት (ነገረ መለኮት) አስተምህሮት መሠረት ክርስቲያኖች ደህንነታቸው መጠበቅ አለበት ምክንያቱም መንፈሳዊና አካላዊ ህይወት የማይነጣጠሉና የማይለያዩ ተጨባጭና ነባራዊ ሁኔታ አላቸው፡፡ የምዕመናኖች ደህንነታቸው የሚተረጎመው አካላዊ ጤና እና በኢኮኖሚ ብልፅግና ይገለፃል፡፡ የብልጽግና ነገረ መለኮት መምህሮች አትኩሮቱን ለግለሰብ ሥልጣን መስጠት በመንፈሳዊና አካላዊ ጥምረት በጎ ጎን በመገንባት ያሳልፋል፡፡ ክርስቲያኖች በተፈጥሮ ላይ ሥልጣን ተሰጥቶቸዋል ምክንያቱም ክርስቲያኖች በእግዚአብሄር አምሳያ ስለተፈጠሩ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ዓለማቸውን በማለማመድ በአካባቢያቸው የሚገኙ ቁስአካላዊ ነገሮች መጠቀም መቻል አለባቸው፡፡ የብልጽግና መንፈሳዊ ትምህርት መሪዎች ያለ አንዳች ፀፀት ኃጢአታችንን እንዲያስተሰርይልን፣ ከበሽታ ደዌን ለመፈወስ፣ ከድህነት አረንቆ ለመላቀቅ፣ ከመንፈሳዊ እርኩስነት ለመንፃት፣ ድህነትና በሽታ በህብረተሰቡ ዘንድ እንደእርግማን ስለሚቆጠር በእምነትና በእውነት ይህን የተሳሳተ አስተሳሰብ መስበር እንችላለን፡፡ ”Prosperity theology teaches that Christians are entitled to well-being and, because spiritual and physical realities are seen as one inseparable reality, interprets well-being as physical health and economic prosperity.[47] Teachers of the doctrine focus on personal empowerment,[48] promoting a positive view of the spirit and body. They maintain that Christians have been given power over creation because they are made in the image of God and teach that positive confession allows Christians to exercise dominion over their souls and material objects around them.[48] Leaders of the movement view the atonement as providing for the alleviation of sickness, poverty, and spiritual corruption;[49] poverty and illness are cast as curses which can be broken by faith and righteous actions.” 2
የዘመናዊ ሽብርተኛነት ታሪካዊ አጀማመር ከፈረንሳይ አብዬት ጋር ይያያዛል፡፡ በዘመኑ የሽብርተኛነት ሥር መሠረቱ መንስዔው ሥልጣኔ አሊያም የባህል ግጭቶች፣ ዓለም አቀፋዊ ትሥሥር፣ ኃይማኖታዊ ግጭቶች፣ የእስራኤልና የፓልስታይን ግጭት፣ አሊያም የራሽያ አፍጋኒስታን መውረር በሃገራት መህል የተከሰቱ ሽብርተኞነት ያካትታል፡፡ የዘመናዊ ሽብርተኛነት በግለሰብ ደረጃ በስብዓናችን ላይ የሚከሰት ብስጭት፣ የመገለል ስሜት፣ አሉታዊ የማንነት ጥያቄ፣ ራስን ማፍቀርና ማምለክ ንዴት እና ወይም የግብረገብነት ፈሪሃ እግዜብሄር ጋር ያለ ግንኙነት መላሸቅ ስሜቶች ይካተታሉ፡፡ በሃገራችን ኃይማኖታዊ ግጭቶች ወደ ዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጀጆኖሳይድ) ተሸጋግሮል፡፡
Prosperity theology (sometimes referred to as the prosperity gospel, the health and wealth gospel, the gospel of success, or seed faith)[A] is a religious belief among some Protestant Christians that financial blessing and physical well-being are always the will of God for them, and that faith, positive speech, and donations to religious causes will increase one’s material wealth.[1] Prosperity theology views the Bible as a contract between God and humans: if humans have faith in God, he will deliver security and prosperity.[2]
The doctrine emphasizes the importance of personal empowerment, proposing that it is God’s will for his people to be blessed. The atonement (reconciliation with God) is interpreted to include the alleviation of sickness and poverty, which are viewed as curses to be broken by faith. This is believed to be achieved through donations of money, visualization, and positive confession.
It was during the Healing Revivals of the 1950s that prosperity theology first came to prominence in the United States, although commentators have linked the origins of its theology to the New Thought movement which began in the 19th century. The prosperity teaching later figured prominently in the Word of Faith movement and 1980s televangelism. In the 1990s and 2000s, it was adopted by influential leaders in the Pentecostal movement and charismatic movement in the United States and has spread throughout the world. Prominent leaders in the development of prosperity theology include E. W. Kenyon,[3] Oral Roberts,[4] A. A. Allen,[5] Robert Tilton,[6] T. L. Osborn,[7] Joel Osteen, Creflo Dollar,[8] Kenneth Copeland,[9] Reverend Ike,[10] and Kenneth Hagin.[11]
Prosperity theology has been criticized by leaders from various Christian denominations, including within the Pentecostal and charismatic movements, who maintain that it is irresponsible, promotes idolatry, and is contrary to scripture. Secular as well as some Christian observers have also criticized prosperity theology as exploitative of the poor. The practices of some preachers have attracted scandal and some have been charged with financial fraud.
(From Wikipedia, the free encyclopedia) 2
የኦሮሚያ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ ብልፅግና ፓርቲ መሪ ዶክተር ዐብይ አህመድ ሥልጣን መንበሩን በመጋቢት 10 ቀን 2010ዓ/ም ከያዘ ጀምሮ በኢትዮጵያ የዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) የተካሄደባቸው ዜጎችን ሁሉ ‹‹እግዜር ያፅናችሁ›› እንኳን ለማለት ያልደፈሩት ከሚከተሉት የብልጽግና መንፈሳዊ ትምህርት (ነገረ መለኮት) አስተምህሮት በጎ ነገሮችን ብቻ ማስብና ማስላሰል፣ ስለ ብልፅግና የልማት መንገድ፣ የመሠረተልማት እድገት፣ ስለከባቢ ዓየርና ስለ ዕፅዋቶች፣ ስለ እንሰሳት፣ ስለ ሰማየ ሰማያቱና ከዋክብቱ፣ በማሰብ እንደ መግነጢስ ኃብትን ንብረትን፣ ጤንነትን፣ ፍቅርንና ወንድማማችነትን፣ ነፃነትንና መብትን፣ ስብዓዊነትንና ዴሞክራሲን በመንፈሳችን በመሳብ በእውን ተግባራዊ እንዲሆን ፈጣሪያችን ይረዳናል፡፡ ስለዚህ መጥፎ ነገሮችን፣ ግድያ ሞት፣ ኃዘን፣ ርሃብና ስደት፣ ድንቁርናና እርዛት፣ በሽታና ደዌ፣ ፀብና ጦርነት፣ ወዘተ በህሊናችን ማሰብና ማሰላሰል ክፉ ድርጊቶች ክስተት በመሳብ በእውኑ ዓለም ይፈጸማልና መሸሽ አስፈላጊ ነው ብሎ የማመን የብልጽግና ነገረ መለኮት ተከታዬች እምነት ነው፡፡ ለዚህ ነው ዶክተር ዐብይ አህመድ ዓይተው እንዳላዩ፣ ሰምተው እንዳልሰሙ በመሆን ባንዲራ ሳያወርዱ የሚተውኑት፡-
- በ2011 ዓ/ም የጁዋር መሃመድ የተከብቢለሁ የ86 (ሰማንያ ስድስት) ሰዎች ሞት፣ ንብረት ውድመትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ወንጀሎች ተፈፅመዋል፡፡ ዶክተር አብይ የሞቾችን 82 ወንድና አራት ሴት፣በብሔር ሽንሸና ሃምሳ ኦሮሞ፣ ሃያ አማራ፣ ስምንት ጋሞ፣ ሁለት ስልጤ፣ አንድ ጉራጌ፣ ሁለት ሃድያ፣ አንድ አርጎነባና አንድ ብሄሩ ያልታወቀ፡፡ በሃይማኖት አርባ ክርስቲያን፣ ሠላሳ አራት ሙስሌም፣ አስራሁለት የሌላ እምነት ተከታይ ናቸው፡፡ ሰባስድስት በእርስበእርስ ግጭት የሞቱ፣ አስር በፀጥታ ኃይሎች እንደተገደሉ አስታውቀው ነበር፡፡
- በ2012 ዓ/ም ሃጫሉ ሁንዴሳ 187 ሰዎች ተገድለዋል የኦነግ ቄሮ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ቄሮ ድርጅታዊ የዘር ፍጅት ተዋናዬች በነፃና ገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለፍርድ ይቅረቡ!!! በዚህ የህቡዕ መፈንቅለ መንግሥት የፖለቲካ ሴራ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ምክንያት የተደገሠው የዘር ፍጅት ሁለት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ሰዎች ሞት፣ ሁለት መቶ ሰዎች መቁሰል፣ ሁለት መቶ ሃምሳ መኪኖች መሰባበርና ሃያ መኪኖች መቃጠል፣ የአርባ አምስት ፎቆች መቃጠል፣ ብዙ ሽህ ቤቶች መቃጠል፣ መሠረቱ በዘርና በኃይሞኖት የማንነት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የመንግሥት ሥራ ሲሆን በአመዛኙም የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ሠራዊቱና የፀጥታና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች እንዲሁም የክልል ሹማምንቶች የኦዴፓ/ብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች ሃላፊነትና ተጠያቂነት መኖር አለበት እንላለን፡፡ ዓለም አቀፍ ትብብር በኢትዮጵያ መብት ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችንና ዲያስፖራውን አስተባብረው አይሲሲ በገለልተኛ ተቆማት ፍርድ እንዲሰጥ ማድረግ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው እንላለን፡፡
- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፡- ከዘር ፌዴራሊዝም ወደ ደም ፌዴራሊዝም !!! አጋንቱን አራጅ ከብልቃጡ ውስጥ ይዱሉት!!! ‹‹የአማራ ማስሚዲያ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ ዜና መሠረት ጳጉሜ አንድ ቀን 2012ዓ/ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዘር ተኮር ፍጅት (ጆኖሳይድ) በመተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ኤባር ተብሎ የሚጠራ ቀበሌ አማራና አገው ሰማንያ ዘጠኝ ተወላጆች ላይ በስም ዝርዝር ተጠቁመው አሰቃቂ ዘር ተኮር ግድያ ተፈፅሞል፡፡ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ውስጥ የቤሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ (ቤህን)፣ ጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉዴን) ከ ኦነግ ሸኔ ጋርና ከህወሓት ስውር እጅ ጋር በመጣመር የዘር ፍጅቱን አድርገዋል፡፡ የወረዳው ፖሊስ አስቀድሞ ቀበሌውን ለቆ ወጥቶ ነበር፡፡ በአለፈው ጊዜም ሃያ አምስት ሽህ የአማራና አገው ተወላጆች ተፈናቅለው እንደነበር የታወሳል፡፡ በ1983ዓ/ም ኦነግና ሻብያ የዛሬ ሠላሳ አመት በቤኒሻንጉል አሶሳ ሆስፒታልና ትምህርት ቤት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው እንደተቃጠሉ በታሪክ ይታወሳል፡፡››1
- በ2013 ዓ/ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በመገዝ ቀበሌ በታጣቂዎች 21 ሰዎች መገደላቸውን ታውቆል፡፡ ሞቾቹ ተፈናቅለው የነበሩ ወደ ቀበሌቸው ተመልሰው የሰፈሩ ሰዎች መሆናቸው አሳዛኝ ሆኖል፡፡
ዶክተር ዐብይ አህመድ የሁሉንም ሃይማኖት እምነት ተከታዬች በእኩልነት እንደማያዩ በተለይም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለውጥ የማይቀበል፣ የብልጽግና ልማት እድገት የማይደግፍ በተፈጥሮው ፀረ-ለውጥ አቆም ያለው ኃይማኖት ነው በማለት በመንግሥታዊ ኮንፍረንስ ላይ በተሰራጨ ማንዋል ተገልፆ ነበር፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የሚፈፀም የዘር ማጥፋት (ጆኖሳይድ) ታሪካዊ መረጃዎች አሉ፡፡
በ1982 ዓ/ም መግቢያ ላይ፣ ህወሓት ሥልጣን ከመያዙ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ፣ በአሶሳ ከተማ ኦነግና ሻዕቢያ የተሳተፉበት ክርስቲያኖችንና አማራዎች የሚሏቸውን ለይተው ቤት ዘግተው በእሳት ማቃጠላቸው የሕዝቡ መፃዒ ዕድል ምን ሊሆን እንደሚችል አመላካች አሰቃቂ ተግባር ነበር። በሻብያና በኦነግ የተፈፀመ የዘር ጭፍጨፋ ነበር፡፡ ሻብያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂና ሌንጮ ለታ በጆኖሳይዱ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ በ1984/85 ዓ/ም በአርሲ ሃገረ-ስብከት አርባጉጉ አውራጃ በ680 ካህናትና ኦርቶዶክሳዊያን በአሰቃቂ አረመኔዊ ተግባር ታርደዋል፣ ተቃጥለዋል ከገደል ላይ ተወርውረዋል፡፡ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፣ ቅርሶች ተዘርፈዋል፣ አርባ ሦስት ሽህ ምዕመናን ተሰደዋል፡፡ በምዕራብ ሐረርጌ ሃገረስብከት አሰቦት ገዳምና አቡነ ሣሙኤል ገዳም መነኮሳትና ምዕመናን በግፍ ታርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፡፡ 1998 ዓ/ም በህዳር 8 እና 9 ቀን፣ በአርሲ ሃገረስብከት ኮፈሌ ቆሬ ከተማ አይሻ ሰበካ ስድስት ምዕመናን ተገለዋል፡፡ ከመቶ በላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ተከታዬች ቤታቸው ተቃጥሎ ተሰደዋል፡፡ የማርያም ቤተከርስቲያን ተቃጥላለች፡፡ 1999 ዓ/ም ከመስከረም እስከ ጥቅምት አምስት፣ በሻሻ ዴዴሳና በሞናቶ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ተቃጥሎል፡፡ካህናትና ምዕመናን ታርደዋል፣ የምዕመናን መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ ለተጨማሪ ግንዛቤ ከድረ ገፁ እንድታነቡ ተጋባዛችሆል፡-
There are, however, some prosperity churches which seek a more moderate or reformed paradigm of prosperity.[11] Kirbyjon Caldwell, pastor of a Methodist mega-church, supports a theology of abundant life, teaching prosperity for the whole human being, which he sees as a path to combating poverty.[8][B] Wealth is interpreted in prosperity theology as a blessing from God, obtained through a spiritual law of positive confession, visualization, and donations.[50] Believers may see this process in almost mechanical terms;[51]
Kenneth Copeland, an American author and televangelist, argues that prosperity is governed by laws,[9] while other teachers portray the process formulaically.[49] Journalists David van Biema and Jeff Chu of Time have described Word of Faith pastor Creflo Dollar‘s teachings about prosperity as an inviolable contract between God and humanity.[8]The prosperity theology teaching of positive confession stems from its proponents’ view of scripture. The Bible is seen as a faith contract between God and believers; God is understood to be faithful and just, so believers must fulfill their end of the contract to receive God’s promises. This leads to a belief in positive confession: the doctrine that believers may claim whatever they desire from God, simply by speaking it. Prosperity theology teaches that the Bible has promised prosperity for believers, so positive confession means that believers are speaking in faith what God has already spoken about them. Positive confession is practiced to bring about what is already believed-in; faith itself is a confession, and speaking it brings it into reality.[52]
The teaching often depends on non-traditional interpretations of Bible verses,[49] the Book of Malachi often being given special attention. While Christians have generally celebrated Malachi for its passages about the Messiah, teachers of prosperity theology usually draw attention to its descriptions of physical wealth.[53]
- የሃይማኖትና፣የእምነትና የአመለካከት ነፃነት አንቀጽ ሃያ ሰባት መሠረት
አንደኛ ‹‹ማንኛውም ሰው የማሰብ፣ የሕሊና እና የሃይማኖት ነፃነት አለው፡፡ ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል ፣ ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣ የመተግበር ፣ የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል፡፡››
ሁለተኛ ‹‹በአንቀጽ ፺ ንዑስ አንቀጽ 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሃይማኖት ተከታዬች ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋትና ለማደራጀት የሚያስችሏቸው የሃይማኖት ትምህርትና የአስተዳደር ተቌማት ማቌቌም ይችላሉ፡፡››
አንቀጽ ፺ ‹ማህበራዊ ነክ ዓላማዎች› ተራ ቁጥር ሁለት ‹‹ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተዕፅኖዎች ነፃ በሆነ መንገድ መካሔድ አለበት፡፡›› ይላል፡፡
ሦስተኛ‹‹ማንኛውም ሰው የሚፈልገውን እምነት ለመያዝ ያለውን ነፃነት በኃይል ወይም በሌላ ሁኔታ በማስገደድ መገደብ ወይም መከልከል አይቻልም፡፡››
አራተኛ ‹‹ወላጆችና ህጋዊ ሞግዚቶች በእምነታቸው መሠረት የሃይማኖታቸውንና የመልካም ሥነ ምግባር ትምህርት በመስጠት ልጆቻቸውን የማሳደግ መብት አላቸው፡፡››
አምስት ‹‹ሃይማኖትንና እምነትን የመግለፅ መብት ሊገደብ የሚችለው የሕዝብ ደህንነት፣ ሰላምን፣ ጤናን፣ ትምህርትን፣ የሕዝብን የሞራል ሁኔታ፣ የሌሎች ዜጎችን መሰረታዊ መብቶች፣ ነፃነቶች እና መንግሥት ከሃይማኖት ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚወጡ ሕጎች ይሆናል፡፡›› 3
- ዓለም አቀፍ ትብብር በኢትዮጵያ መብት ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችንና ዲያስፖራውን አስተባብረዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ( International Crimial Court (ICC) በነፃና ገለልተኛ ተቆማት ፍርድ እንዲሰጥ ማድረግ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው እንላለን፡፡
- የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተቃጠለባቸው፣ ካህናትና ምዕመናን የተገደሉባቸው ስፍራዎች ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ አጣዬ ወዘተ በናሙናነት ይጠቀሳሉ፡፡
- የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዕምነት ቦታዎች የመስቀል ማክበሪያ ቦታዎች በኦነግ/ ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሚያና ደቡብ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በሚገኙ የእምነት ቦታዎች ላይ በተደጋጋሚ የተፈፀመ የሃይማኖት እምነት መብት ጥሰት ተፈፅሞል፡፡ (ደብረዘይት፣ ሆሳዕና ወዘተ)
- የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዕምነት ተከታዬች ካህናትና ምዕመናን ሰላማዊ ሠልፍ (መስከረም አራት 2012ዓ/ም የተጠራውን ሠላማዊ ሠልፍ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ እንዳገደ ይታወቃል፡፡) እንዳያደርጉ መታፈን ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ላይ ይገኛል፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰላማዊ የእንቢተኛነት ትግል፣ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ቢጠሩ ህዝብ ተግባራዊ ያደርጋል እንላለን፡፡
- ‹‹በሀገራችን ውስጥ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ግምባር ቀደም ተጠቂ ይሁኑ እንጂ፣ “መጤ”ና “ኗሪ” በሚል የጥላቻ ትርክት የተቀመረው ሕገ-መንግሥት ሌሎች ብሄረሰቦችንም ለጥቃት አጋልጧቸዋል። ጉራጌዎች፣ ስልጤዎች ጋሞዎች…ወዘተ ተጠቂዎች ሆነዋል። በሃይማኖትም ክርስቲያን ኦሮሞዎች የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ይገኛሉ። በአብዲ ኢሌ የሥልጣን ዘመን ወደ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዜጎቻችን ከሶማልያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ተፈናቅለዋል። በተመሳሳይ መልኩ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሌ ብሄረሰብ ዜጎቻችን ከኦሮሚያ ተፈናቅለው ለስቃይ ተዳርገዋል። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የጌዲዖ ዜጎቻችንም በኦሮሞ ፅንፈኞች ተፈናቅለው በብርድና በዝናብ በመጠለያ ሥፍራዎች እስከ አንድ ዓመት ድረስ ኖረዋል። የፈረደባቸው የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ከቤኒሻንጉል በተደጋጋሚ ተፈናቅለዋል፣ እስከዛሬም ያላቆመ ክስተት ነው።››
- የፌዴሬሽኑን ሕገ-መንግሥትና የክልል ሕገ-መንግሥቶችም፣ ተቀርፀው የተዋቀሩት አንዱን ‹ኖሪ/ባለቤት› የአንደኛ ደረጃ ዜጋ ሌላውን ‹መጤ/ ሠፋሪ› በሚል የሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ማዕከልነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው። በቡራዩ፣ በአርሲ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሻሸመኜ፣ በዝዋይና በባሌ እስከ ሦስት ጊዜ ድረስ የተካሄደው ጥቃት፣ ባመዛኙ የአማራና ሌሎችንም “መጤ” ተብለው የተሰየሙ ብሄረሰብ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞችንና የዕምነት ቤቶችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ነው። በኢትዮጵያ የሃይማኖትና፣የእምነትና የአመለካከት ነፃነት በትግላችን ይከበራል!!! መልካም የመስቀል በዓል ይሁንላችሁ!!! መልካም የኢሬቻ በዓል ይሁንላችሁ!!!
ምንጭ
- Prosperity church logo
- https://en.wikipedia.org/wiki/Prosperity_theology
- የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ገፅ 17፣ 18፣ 63